ለማህበረሰቡ ወቅታዊና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ይሰበስባል : ያደራጃል እንዲሁም ያሰራጫል
የካቢኔ አጀንዳዎች ከመሰብሰብ ጀምሮ እስከ ቅድሚያ መስጠትና መፍትሄ መፈለግ
በማህበራዊ, ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ ውጭ አገር ከተማዎች ጋር ሽርክና ማቋቋም.
አዎንታዊ ለውጥ ለመገንባት አለም አቀፍ ስብሰባዎችንና አውደ ጥናቶች ያደራጃል
የእቅድ ትግበራ ምዘናና ክትትል ማስፈጸም
የእቅድ ትግበራ ያደራጃል ይመረምራል
ዋና ዋና የከተማዋ መልካም አስተዳደርና የልማት ለውጦችን በህትመትና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በኩል ለህብረተሰቡ ማስተዋወቅ
በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ መረጃ ይሰበስባል ያዘጋጃል ይሰጣል
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
የሸገር ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች የአረንጓዳ ልማት ስራዎች ላይ የቴክኒክ እና የገንዝብ ድጋፍ ማድርግ በስምምነቱ ከተካተቱ ጉዳዩች መካከል አንዱ ነው።
Read more...
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራት ክፍለ ከተሞች በ132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ ነው፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ት አለም አሰፋ እንደገለጹት በከተማዋ የመናፈሻ ፓርኮች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ ይገኛል፡፡በቅርቡም የከተማው ካቢኔ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚህም የከተማዋን አረንጓዴነት ያጠናክራሉ የተባሉ እና ለነዋሪዎቿ የመዝናኛ አማራጭ ያሰፋሉ የተባሉ በአራት ክፍለ ከተሞች በሚገኑ 132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ግንባታ ለማካሄድ የመሬት ልየታ ስራ መሰራቱን ወ/ት አለም አሰፋ ተናግረዋል፡፡
Read more...አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ ህብረት ዋና መ/ቤት መቀመጫ ስትሆን በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ባላት ታሪካዊ , ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ትርጉም "የአፍሪካ ዋና ከተማ" የሚል ስያሜ አሰጥቶአታል። የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤትም ከተማይቱ ውስጥ ማግኘት ይቻላል.
ከእንጦጦ ተራሮች ግርጌ ስር የምትገኝ ሲሆን ከባሕር ወለል በላይ 7.726 ጫማ (2,355 ሜትር) በዓለም ውስጥ ሶስተኛው ከፍተኛ ዋና ከተማ ናት.በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥዋ በአገሪቱ ማዕከላዊ ስፍራ ውስጥ ትገኛለች።
Rating:በ 2007 ዓ.ም በተደረገ ቆጠራ ከ 3.627.934 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያላት አዲስ አበባ በዓለም ካሉ በመሬት ከተከበቡ ሀገራት ትልቋ ዋና ከተማ ናት፡፡
ከአለም ውብ ከተማዎች መካክል የምትጠቀሰው ይች ከተማ በታሪክ በጣም ጉልህ የሆነ ስፍራ አላት።
Rating: