open

ቁልፍ ደንበኞቻችንአላማችን የደንበኛ እርካታ ለማግኘት ነው

 

 

 
ነዋሪዎች

ለማህበረሰቡ ወቅታዊና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ይሰበስባል : ያደራጃል እንዲሁም ያሰራጫል

  
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት

የካቢኔ አጀንዳዎች ከመሰብሰብ ጀምሮ እስከ ቅድሚያ መስጠትና መፍትሄ መፈለግ

   
መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
<p〉ዝግጅቶችን ያደራጃል ፡ የፕሮቶኮል አገልግሎቶችን ያቀርባል እንዲሁም አጠቃላይ የማማከር አገልግሎቶችን ይሰጣል

 

 
እህት ከተሞች

በማህበራዊ, ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዓላማዎች ላይ የተመሠረተ ውጭ አገር ከተማዎች ጋር ሽርክና ማቋቋም.

 
ኤምባሲዎች / የዲፕሎማቲክ ድርጅቶች

አዎንታዊ ለውጥ ለመገንባት አለም አቀፍ ስብሰባዎችንና አውደ ጥናቶች ያደራጃል

  
የፌዴራል መንግስት

የእቅድ ትግበራ ምዘናና ክትትል ማስፈጸም

  
የኃይማኖት ተቋማት

የእቅድ ትግበራ ያደራጃል ይመረምራል

   
ሚዲያ

ዋና ዋና የከተማዋ መልካም አስተዳደርና የልማት ለውጦችን በህትመትና የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በኩል ለህብረተሰቡ ማስተዋወቅ

  
ዳያስፖራ

በዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ መረጃ ይሰበስባል ያዘጋጃል ይሰጣል

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ነሀሴ 14 2012 ቀን ስልጣን ተረክበዋል

ታሪካችን!

Latest Blogs

የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ  ብዙ ስራዎች እነደሚሰራ ተናገረ፡፡ September 22
የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ብዙ ስራዎች እነደሚሰራ ተናገረ፡፡
1

በአዲስ አበባ በየካቲት 27 /2011 ዓም. በተደረገው እጣ ማውጣት ስነ-ስርአት እጣ ወቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ በአፋጣኝ የሚፈፀም መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ

=================

የከተማ አስተዳደሩ በየወቅቱ የሚነሱ የነዋሪዎቹን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የጋራ መኖርያ ቤቶች ጉዳይ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ የበዛበት ሆኖ ቆይቶአል፡፡ በቀረበው የስራ ሪፖርት መሰረት ዕጣ ወቶላቸው በባለ እጣዎች እጅ ያልደረሱ ቤቶች መኖራቸውን ማወቅ ተችሎአል፡፡ይኃውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 40/60 እና 20/80 ፕሮግራሞች የተገነቡ ቤቶችን የካቲት 27/2011 / ዕጣ ማውጣቱ እና ሆኖም ቤቶቹ በቂ የመሠረተ ልማት በሌለባቸው የማስፋፊያ አካባቢዎች በመገንባታቸው እና በሚፈለገው ልክ አጠቃላይ የሳይት ስራው በወቅቱ ባለመጠናቀቁ ለባለ እድለኞች ሳይተላለፉ መቆየታቸውን የከተማው አስተዳደርሩ ገልፆ እጣ ወቶላቸው ውል ላልገቡ እና ቁልፍ ላልተረከቡ ባለ ዕጣዎች ውል ማስገባትና ቁልፍ ማስረከቡ እንዲጀመር ወስኖአል።

Read more...
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ደርሰዋል። September 21
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ደርሰዋል።
10

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል በወንዞች ሙላት ሳቢያ በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በአይነት 10 ሚልዮን እና በገንዘብ 2 ሚልዮን በድምሩ 12 ሚልዮን ድጋፍ ለማድረግ የከተማው ካቢኔ መወሠኑ ይታወሳል።በዚህም መሰረት ስጦታውን ለማድረስ ወደ አፋር ተጉዘዋል፡፡

በስጦታ ርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክልሉ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ባይጠፋም በደረሰው የመፈናቀል እና የዜጎች መንገላታት ማዘናቸውን ገልጸዋል።የአዲስ አበባ የሁሉም ዜጎች መኖሪያ እንደመሆኗ በአፋር ክልል በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በዜጎች ላይ የደረሰው ችግር የሁላችንም ችግር ነውም ብለዋል፡፡በደረሰው አደጋ ለተጎዱ እና ከመኖሪያ ቄያቸው ለተፈናቀሉ የአፋር ወገኖቻችን የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የዘለቀውን የመደጋገፍና የመተባበር እሴቶችችንን የሚያዳብር እና አብሮነትን የሚያረጋግጥ እንደሆነም / አዳነች ተናግረዋል፡፡

Read more...


ስለ አዲስ አበባ  ፈጣን እውነታዎች