open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

ባለፉት ስድስት ወራት 1383 በላይ የህዝብ ቅሬታዎች ለጽህፈት ቤቱ ቀርበው መፍትሄ አግኝተዋል፡፡
በከተማዋ የተጀመሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት 2012 በጀት ዓመት 6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም የበላይ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ገምግሟል፡፡ በግምገማ መድረኩ የጽህፈት ቤቱ ሓላፊ / አለምፅሐይ ጳውሎስ በከተማዋ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ተግባራዊ ተደርገው አመርቂ ውጤቶች መመዝገቡን ገልፀዋል ፡፡
በተለይ በትምህርት ቤቶች ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን መፍጠር የተማሪዎች ምገባ፣የተማሪዎች የደንብ ልብስ እና የመማሪያ ቁሳቁስ አቅርቦት እና ሌሎች ስራዎችን በዘላቂነት ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ሴክተር ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ሓላፊዋ ተናግረዋል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እስከ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ምስል መለየት የሚያስችሉ የደህንነት ካሜራዎችን ለመግጠም እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ቴክኖሎጂውን መዘርጋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ጀማል በከር የዜጎችን ደህንነት በቴክኖሎጂ ለማስጠበቅ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ቴክኖሎጂው ዜጎች ከደህንነት ስጋት ተላቀው የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዲከውኑ ያግዛል ብለዋል፡፡