open

በጽ/ቤቱ የ2011 ዓ.ም የበጀት ፍላጎትና አዘገጃጀትን አስመልክቶ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ልዮ ልዮ/በጽ/ቤቱ የ2011 ዓ.ም የበጀት ፍላጎትና አዘገጃጀትን አስመልክቶ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል

በጽ/ቤቱ የ2011 ዓ.ም የበጀት ፍላጎትና አዘገጃጀትን አስመልክቶ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል

 

(አዲስ አበባ፣ከንቲባ ጽ/ቤት) የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከጽ/ቤቱ ልዩ ልዩ ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ከሰላሳ በላይ ሰልጣኞች ተካፍለውበታል፡፡

 

ስልጠናውን የሰጡት የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፉ ውቤ አለሙ ሲሆኑ በስልጠናው በ2011 በጀት ዓመት የበጀት ፍላጎት ማቅረብ እና የ2011 በጀት ዓመት አመታዊ የበጀት አዘገጃጀትን አስመልክቶ የቀረቡ ይዘቶች ተካተውበታል፡፡

 

በቀረበው ሰነድም የበጀት ፍላጎት ማለት ወደፊት የሚሰራውን ወይም ይሳካል ተብሎ የሚታለመውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ በጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤ በአግባቡ በማቀድና በመበጀት ለሚቀጥለው አመት የሚሰራው ስራ ምን ያህል በጀት ያስፈልገዋል ብሎ መወሰን ማለት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

 

ከእቅድ ውጭ አቅዶ በጣም የተትረፈረፈና ተመላሽ የሚደረግ በጀት ማስያዝ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም በላይ ሌሎች የሚሰሩ ተቋማትን ገንዘብ አንቆ እንደመያዝ ይቆጠራል ሲሉም አቶ ተስፉ  አስረድተዋል፡፡

 

አቶ ተስፉ አያይዘውም በጀት ውስንነት ያለው በመሆኑ የሚሰራውን ያህል ማቀድና መበጀት አስፈላጊ እንደሆነ በማስረዳት፤ ተመላሽ የሚደረግ በጀት ሁልጊዜ በሚቀጥለው ሲበጀት በፊት ከሚበጀተው ተቀንሶ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

 

በቀረቡት ሁለት ሰነዶች ላይም ከተሳታፊዎች ሃሳብና ጥያቄዎች ተነስተው በተሳታፊዎቹ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

 

Read 584 times