open

የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ጽ/ቤትን የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ገመገመ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ልዮ ልዮ/የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ጽ/ቤትን የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ገመገመ

የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ጽ/ቤትን የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ገመገመ

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከንቲባ ጽ/ቤት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከዕቅድ አንፃር ያከናወናቸውን ስራዎች ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም   በጽ/ቤቱ ስር ከሚገኙ ሁሉም ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከአስሩም ክፍለ ከተሞች የቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤቶች የመጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ የICT አዳራሽ ግምገማውን አካሂዷል፡፡

 

በግምገማው የከንቲባ ጽ/ቤት የዘጠኝ ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በተጨማሪም የህዝብ ቅሬታ አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት  በህዝብ ቅሬታ አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተክሌ ዲዶ ለቋሚ ኮሚቴው ቀርቧል፡፡

 

በተለይ በመልካም አስተዳደር ችግር ህዝቡ የሚያነሳቸው አቤቱታዎች እጅግ በጣም ብዙ በመሆናቸው፤ በክፍለ ከተሞች ከቀረቡት 3ሺህ 5 መቶ ስልሳ አቤቱታዎች 3ሺህ 3 መቶ ያክሉ ምላሽ ማግኘታቸውን፣ በከንቲባ ጽ/ቤት ከቀረቡት 1ሺህ 2 መቶ ዘጠና ስምንት ቅሬታዎች 1ሺህ 2 መቶ አምሳ አራቱ ምላሽ እንደተሰጠባቸው ይህም የዕቅዱን 94.64 ከመቶ መፈጸሙን፣ 44 ያህሉ ለቀጣይ ሩብ ዓመት መሸጋገራቸውም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ ይህ ስራ ከዕቅድ አንፃር ተከናወነ  እንጂ ከዕቅዱ ውጪም በርካታ ስራዎች መከናወናቸውንም አቶ ተክሌ በሪፖርቱ ገልፀዋል፡፡

 

Read 384 times