open

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በ175 ሚሊዮን ብር ባለ ሁለትና አራት እግር ተሸከርካሪዎች ርክክብ ተፈፀመ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ልዮ ልዮ/የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በ175 ሚሊዮን ብር ባለ ሁለትና አራት እግር ተሸከርካሪዎች ርክክብ ተፈፀመ

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በ175 ሚሊዮን ብር ባለ ሁለትና አራት እግር ተሸከርካሪዎች ርክክብ ተፈፀመ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር የገዛቸዉን 307 የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ምለአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በሚሊንዬም አዳራሽ ርክክብ ፈፅሟል፡፡

በርክክቡ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከነቲባ ዶክትር ኢንጂኔር  ሰሎሞን ኪዳኔ እንዳሉት በከፍተኛ ሁኔታ የሰዉ ሕይወትና ንብረት ጥፋት የሚያስከትለዉ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከተማ አስተዳደሩ ብዙ ስራዎችን እየሰራ አንደሚገኝና የትራፊክ ፖሊሶች በፍትነትና በቅልጥፍና በየትኛዉም አካባቢ ተደራሽነታቸዉን ለማስፋት 275 ሞተር ብስክሌቶች፣ 26 ሚኒባሶች፣ አራት ፒክ አፖች፣ ሁለት አምቡላንሶች ግዥ ፈጽሞ በዛሬዉ እለት አስረክቧል ብለዋል፡፡ ምክትል ከንቲባዉ አያዘዉም የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳሮችን፣ ከመጠን በላይ ጠጥቶ መሽከርከር የትንፋሽ መመርመሪያዎችን፣ አፕሊኬሽን የተሞላላቸዉ  ሞባይሎችንም በጭለቱ አስረክቧል ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዉ በመልዕክታቸዉ መሳሪያዎቹንና ተሽከርካሪዎቹን ገዝቶ ማስረከብ ብቻዉን ለዉት እንዳልሆነና የትራፊክ ፖሊሶች ጥብቅ ዲሲፕሊንና በቂ የክህሎት ስልጠና ታግዘዉ ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል የሰዉ ሕይወት የሚቀጥፈዉን የትራፊክ አደጋ መቀነስ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የትራፊክ ፖሊሶች የተሸከርካሪ ትርኢት በማድረግ፣ በማርች ቡድን ጣዕመ ዜማዎች በማጀብ የቁልፍ ርክክቡ ተከናዉኗል፡፡ የስልክ አፕሊኬሽንና የትንፋሽ መመርመሪያ አጠቃቀምና አተገባበራቸዉን በባለሙያዎች የተብራራ ሲሆን ከዚህ በፊት የተሰጡ የክህሎት ማሟያ እና የIT ሥልጠናዎችን የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን ተካሂዷል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በፊትም የትራፊክ ፍሰቱን ለማቀላጠፍ የመንገድ ማዘመን ስራ፣ ተደራራቢ የሸገርና የአንበሳ ከተማ አዉቶቡስ ባመግዛት፣ የቀላል ባዉር በማስገባትየፍጥነት ወሰን ስራ፣ የፍጥነት መቀነሻ ብሬኮችን ተግባራዊ በማድረግ ትልቅ ስራ መሰራቱንና የBRT ፕሮግራምን ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በሪፖርት ተገልጿል፡፡  

 

Read 544 times Last modified on Donderdag, 09 Augustus 2018 06:02