open

ልማዳዊ አሰራርን ወደ ዘመናዊ አሰራር በመለወጥ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት/ልማዳዊ አሰራርን ወደ ዘመናዊ አሰራር በመለወጥ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል

ልማዳዊ አሰራርን ወደ ዘመናዊ አሰራር በመለወጥ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል

(አዲስ አበባ፣ ለከንቲባ ጽ/ቤት) የከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኞች የ2010 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገምና የ2011 የበጀት አመት ዕቅድን በተመለከተ ሐምሌ 19 እና 20 በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ተወያይተዋል፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ አያና  እንዳሉት ለከተማ ለውጥ የከንቲባ ጽ/ቤት ከዝቅተኛ ባለሙያ እስከ ከፍተኛ አመራር በቁርጠኝነት በመነሳት በ2010 ዓ.ም የነበሩ ጉድለቶችንና በበጀት ዓመቱ ያልተሸፈኑ ስራዎችን ወደ 2011 በጀት አመት በማስተላለፍ በዚህ በጀመርነው 2011 በጀት ዓመት ከዘልማዳዊ አሰራር ወጥተን ወደ ዘመናዊና ቀልጣፋ የስራ እንቅስቃሴ በመሸጋገር ውጤታማ ስራ በመስራት በከተማ ያሉ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየተዋረዱ በመፍታት ህብረተሰቡን ማገልገል፣ ብሎም በሁሉም መስክ ውጤታማ ስራ ማስመዝገብ አለብን ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በከንቲባ ጽ/ቤት ስር የሚገኙ 11 የሚሆኑ የዳይሬክቶሬት ጽ/ቤቶች፣ የስራ ክፍሎች ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርቱም ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች፣አስተያየቶችና ገንቢ ሀሳቦች ቀርበውባቸዋል፡፡ የከንቲባ ጽ/ቤት የስትራቴጅክ ዕቅድ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋ ውቤም በ2011 በጀት ዓመት ጽ/ቤቱ በዋናነት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራባቸዋል ተብለው የታቀዱትን ዋና ዋና ተግባራትና ግቦችን አቅርበዋል፡፡ በቀረቡትም ነጥቦች ላይ የተለያዩ ሐሳቦችና ጥያቄዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡በመጨረሻም ሁሉም ክፍሎች የየራሳቸውን ዕቅድ ከክፍል ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች  ጋር ተወያይተው ካስኬድ በማድረግ መስራት እንደሚገባ አቶ ተስፉ ውቤ አሳስበዋል፡፡

 

Read 377 times
More in this category: ዘመናዊ አውቶቢሶች »