open

ምክትል ከንቲባዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ምክትል ከንቲባዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ምክትል ከንቲባዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ  ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሚድያዎች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫዉ ያነሷቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮችም በቢሮ ደረጃ የተጀመረዉ ሪፎርም አስከ ታችኛዉ መዋቅር  ተግባራዊ እንደሚሆን፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉን የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ሥራ እንደሚያከናዉኑ፣ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የቤት ልማት ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ከነበረዉ አሰራር በተለየ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ አዲስ የቤት ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም የነዋሪዎች መታወቂያ ወደ ዲጂታል ካርድ እንደሚቀየር፣ ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡን እያማረረ የሚገኘዉን በተለይ የዉሃን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን እና መሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ኦዲት የማድረግ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር በእለቱ ለተገኙ ጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡

 

 

 

Read 412 times