open

የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የአዲስ አመት ስጦታ አበረከቱ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ማህበረሰብ/የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የአዲስ አመት ስጦታ አበረከቱ

የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የአዲስ አመት ስጦታ አበረከቱ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች፣ ከተማ አስተዳደሩ በሚሊንየም አዳራሽ ባሰናዳውና ‹‹የአዲስ አመት ስጦታ ለእናት ሀገሬ›› በሚል - መሪ ቃል፣ ለአራት ቀናት  በሚቆየው ዝግጅት ላይ  ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ተገኝተዉ ስጦታቸዉን ለወገኖቻቸዉ አበርክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የመማሪያ ቁሳቁስ እና ምግብ አጥተዉ ትምህርታቸዉን በአግባቡ መከታተል ያልቻሉ 30 ሺህ ተማሪዎችና ሌሎችም እርዳታ የሚስፈልጋቸዉ 7 ሺህ ያህል ዜጎች መኖራቸውን በቅርቡ የተጠና ጥናት ያመለክታል፡፡ በመሆኑም የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የተጀመረዉ በጎ ሥራም ተጠናክሮ እየተካሄደ ሲሆን የዚሁ አካል የሆነው የበጎነት ተግባርም ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ.ም የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በኮሚቴዎቻቸዉ አማካኝነት ከቤቶቻቸዉ ያሰባሰቧቸውን ከ3 መቶ በላይ የአዋቂ አልባሳት፣ ከ1መቶ በላይ የህፃናት አልባሳት፣ ጫማዎችና የመማሪያ ቁሳቁሶችን እንዲሁም ከ13 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ሰጥተዋል፡፡ በተያያዘም ቀይ መስቀል ባዘጋጀዉ የደም ማሰባሰብ መርሀ-ግብር ላይ  የደም ልገሳም አካሂደዋል፡፡

በዕለቱ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ታላላቅ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አርቲስቶችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ተገኝተዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩም ያመጡትን የመማሪያ ቁሳቁስ አበርክተዋል፡፡ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማም ደብተርና የለበሱትን ኮት አዉልቀዉ የሰጡ ሲሆን ከቤታቸው አዘጋጅተው ያመጡትን ልብስም በመስጠት አርዓያነታቸዉን አሳይተዋል፡፡

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባና የኤፌዴሪ የኮርያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ድሪባ ኩማም በእንግድነት ተገኝተዋል፡፡ የአዲስ አመት ስጦታ ፕሮግራሙም ከነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ለአራት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

 

Read 583 times