open

የልማት ተነሺዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ማህበረሰብ/የልማት ተነሺዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

የልማት ተነሺዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

1991 ጀምሮ ከፍልውሃ አከባቢ ለልማት ተነስተው ገርጂ ልዩ ስሙ በአልታድ እና የተለያዩ አከባቢዎች ለሚኖሩ 1 452 አባወራዎች የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡
በልማት ምክንያት ከፍልውሃ እና አከባቢው የተነሱ 1 452 አባወራዎች በፈረሱ ቤቶች ምትክ በአልታድ አከባቢ ለረዥም ጊዜያት የኪራይ ቤት ተሰጥቷቸው ሲኖሩ ቆይተዋል፡፡

ተነሺዎቹ በቀድሞ መኖሪያቸው የይዞታ ማረጋገጫ የነበራቸው ቢሆንም በአልታድ በተሰሩ ቤቶች የይዞታ ማረጋጫ ስላልተሰጣቸው ለዓመታት ለአስተዳደራዊ ችግሮች ሲዳረጉ ቆይቷል፡፡

ነዋሪዎቹ ለዓመታት ቅሬታቸውን ለከተማ አስተዳደሩ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መረጃዎችን በማደራጀት የህዝቡን ቅሬታ ለመቅረፍ ጥናት ሲያደርግ መቆየቱን / ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

ከፍል ውሃ የተነሱት የልማት ተነሺዎቹ ለከተማዋ የተሻለ ልማት የመኖሪያ መንደራቸውን በመልቀቃቸው / ታከለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በአልታድ አከባቢ የተገነቡ ቤቶች በኪራይ እየኖሩበት ላሉ ሰዎች እንዲተላለፍ እና የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሠጣቸውም በከተማው ካቢኔ መወሰኑን / ታከለ ኡማ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሰረት 1 ሺህ 452 ለሚሆኑ የአልታድ አከባቢ አባዎራዎች እያንዳንዳቸው የይዞታ ማረጋገጫ የሚሠጣቸው ይሆናል፡፡

ነዋሪዎቹም የከተማ አስተዳደሩ ለዓመታት ጥያቄያቸው ምላሽ በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

 

Read 123 times