open

ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ

ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ

 

ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ህዳር 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም አስቻለው እንደገለጹት ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል፡፡የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በሁሉም ተቋማት የእቅድ ግምገማ አድርገው ጥንካሬ እና ድክመታቸውን በእቅዳቸው ሊሰሩ የሚችሉ ግቦች ላይ ተፈራርመው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሰረት በ41 ተቋማት ላይ የሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማድረግ ለተቋማቱ ደረጃ ሰጥቷል፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ ከነገ ከህዳር 19-20 ቀን 2012 ዓ.ም በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ ተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን አራት ተቋማት ትምህርት ቢሮ ፣ቤቶች እና ኮንስራክሽን ቢሮ ፤የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ እንደሚያቀርቡ አቶ አዲስአለም ተናግረዋል፡፡

 

Read 78 times Last modified on Maandag, 02 Desember 2019 08:13