open

በአዲስ አበባ ከተማ 200 መቶ የእሳት ማጥፊየ ውሀ መቅጃ መሳሪያዎች ሊተከሉ ነው

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት/በአዲስ አበባ ከተማ 200 መቶ የእሳት ማጥፊየ ውሀ መቅጃ መሳሪያዎች ሊተከሉ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 200 መቶ የእሳት ማጥፊየ ውሀ መቅጃ መሳሪያዎች ሊተከሉ ነው

 

ሁለት መቶ የእሳት ማጥፊያ ውሃ መቅጃ መሣሪያዎች /fire hydrants /በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ሊተከሉ ነው ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከከተማ እና ከህንፃዎች ዕድገት ጋር ተያይዞ እየሰፋ ከመጣውን የእሳት እና ተያያዥ አደጋዎች ለመቀነስ የእሳት ማጥፊያ የሚያገለግሉ ሁለት መቶ የውሃ መቅጃ መሣሪያዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

 

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ እንደገለፁት የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎቹ(fire hydrants) 8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ ሲሆን፣ ከከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ቦታዎች ይተከላሉ።

 

የእሳት አደጋ ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ውሃ የሚገኘበት ሁኔታ ብቁ ስላልሆነና የከተማው መስፋፋትም የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ያልተተከለባቸው በርካታ አካባቢዎች ስላሉ ቦታዎች ተለይተው እንደሚተከሉ ገልጸዋል፡፡

 

በዋናነት ብዙ ነዋሪዎች ባሉባቸው ሠፋፊ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች፣ በትላልቅ ሆቴሎች አካባቢ እና ፋብሪካዎች ያሉበት አካባቢ ከሚተከሉባቸው ዋናዎቹ መሆናቸውን ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ ጠቁመዋል።

 

ቀደም ሲል ከተተከሉት መካከል አንዳንዶቹ የውሃ ኃይላቸው ያነሰ፤ ውሃ መስጠት የማይችሉ በመሆናቸው ከመንገዶች ባለሥልጣንና ከውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት እንደሚስተካከሉ ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

 

በተለያዩ ቦታዎች ተተክለው የነበሩትን የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች የማደስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ሌሎች የእሳት መከላከያ ማሽነሪዎችም መገዛታቸውንም ገልፀዋል።

 

ከማሽነሪዎች መሟላት በተጨማሪ የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎችን በየጊዜው በሥልጠና የማብቃት ሥራ መሆኑን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

Read 166 times