open

ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማው የግንባታ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ጋር ዉይይት አድርገዋል

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማው የግንባታ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ጋር ዉይይት አድርገዋል

ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማው የግንባታ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አልሚ ድርጅቶች ጋር ዉይይት አድርገዋል

 

 

/ ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን የግንባታ መጓተትና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ዉይይት ከዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር አድርገዋል

በዉይይት መድረኩ ላይ በሶስት ክፍለከተሞች ማለትም በቦሌ አራዳ እና ቂሪቆስ ክፍለከተማ በሚገኙ 17 የሚሆኑ የተለያዩ ግንባታዎች ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡የዉይይቱ ተሳታፊዎች የባንክ ብድር አቅርቦትን ጨምሮ ከሊዝ አዋጅና መመሪያ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር እንዲሁም ሌሎች ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን በዋናነት አንስተዋል።ግንባታዎቹ የከተማው አንጡራ ሀብት ናቸዉ ያሉት / ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 

በዚህም በከንቲባ /ቤት አስተባባሪነት መሬት አስተዳደር ግንባታ ፈቃድ ፕላን ኮሚሽን መንገዶች ባለስልጣን ኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም ከመሠረተ ልማት አገልግሎት አቅራቢ ተቋማት ያሉ ችግሮችን በግንባታ ስፍራዎቹ በመገኘት እልባት የሚሰጥ ቡድን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚቋቋምና ወደ ስራ እንደሚገባም / ታከለ ኡማ ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ አልሚዎችን ጨምሮ የህንጻ ተቋራጮች አማካሪዎች እንዲሁም የባንክ ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

 

Read 53 times