open

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ተከሉ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ተከሉ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ተከሉ

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ችግኝ ተከሉ፡፡የዓለም የምግብ ፕሮግራም 2050 እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 70በመቶ የምግብ አቅርቦት በከተማ ግብርና እንዲሸፈን ፕሮጀክት ቀርፆ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ ግብርና ማደግ የጤናም የኢኮኖሚም ፋይዳ ያለው መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠርም የከተማ ግብርናን ማሳደግ አንዱ መንገዳችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የፖም /አፕል/ ፍራፍሬ ችግኝ ተክለዋል፡፡

 

 

በተያያዘም ከነገ መጋቢት 03 እስከ 07 ቀን 2012 . ድረስ የሚቆይ የአርሶ አደሮች እና የከተማ ግብርና ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተዘጋጅቷል፡፡
በኤግዚቢሽን ማዕከል በሚካሄደው መርሃግብር የዘርፉ ተዋንያን የምርጥ ዘር እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት እንዲሁም በከተማ ግብርና የተሰማሩ ማህበራት ምርቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 57 times Last modified on Vrydag, 13 Maart 2020 07:07