open

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ደርሰዋል።

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ደርሰዋል።

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ሰመራ ከተማ ደርሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአፋር ክልል በወንዞች ሙላት ሳቢያ በተፈጠረው የጎርፍ መጥለቅለቅ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች በአይነት 10 ሚልዮን እና በገንዘብ 2 ሚልዮን በድምሩ 12 ሚልዮን ድጋፍ ለማድረግ የከተማው ካቢኔ መወሠኑ ይታወሳል።በዚህም መሰረት ስጦታውን ለማድረስ ወደ አፋር ተጉዘዋል፡፡

በስጦታ ርክክቡ ወቅት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክልሉ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ባይጠፋም በደረሰው የመፈናቀል እና የዜጎች መንገላታት ማዘናቸውን ገልጸዋል።የአዲስ አበባ የሁሉም ዜጎች መኖሪያ እንደመሆኗ በአፋር ክልል በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በዜጎች ላይ የደረሰው ችግር የሁላችንም ችግር ነውም ብለዋል፡፡በደረሰው አደጋ ለተጎዱ እና ከመኖሪያ ቄያቸው ለተፈናቀሉ የአፋር ወገኖቻችን የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት የዘለቀውን የመደጋገፍና የመተባበር እሴቶችችንን የሚያዳብር እና አብሮነትን የሚያረጋግጥ እንደሆነም / አዳነች ተናግረዋል፡፡

 

በአደጋው የተፈናቀሉ ዜጎች ህይወታቸውን በዘላቂነት እንዲመሩ የከተማ አስተዳደሩ ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋልም ብለዋል።የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሐጂ አወል አርባ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ መጥለቅለቅ የተጎዱ የክልሉ ዜጎችን ለመደገፍ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ድጋፉ አዲስ አበባ የሁሉም ዜጋ መመኪያ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው ያሉት ሃጂ አወል የክልሉ መንግስት ዜጎችን ህይወታቸውን በዘላቂነት እንዲመሩ ለማድረግ በሚሰራው ስራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጎናቸው እንደሚቆም ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል፡፡

 

Read 19 times Last modified on Maandag, 21 September 2020 08:04