open

የ2013 በሆራ አርሰዴ የሚከበረው ኢሬቻ ክብረ በዓል በድምቀት በሠላም ተከበረ ።

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/የ2013 በሆራ አርሰዴ የሚከበረው ኢሬቻ ክብረ በዓል በድምቀት በሠላም ተከበረ ።

የ2013 በሆራ አርሰዴ የሚከበረው ኢሬቻ ክብረ በዓል በድምቀት በሠላም ተከበረ ።

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ በሆራ አርሰዴ በተከናወነ ስነስርዓት ተከበረ።የበዓሉ ስነ ስርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ አርሰዴ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።

 

ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል ሲሆን በዚህ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ምድርንና ሰማይን፣ ወንዝንና ባህርን፣ ቀንንና ሌሊትን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ ሕይወትና ሞትን፣ ክረምትንና በጋን፣ ዝናብንና ሐሩርን፣ ዕጽዋትን፣ እንስሳትንና ሰውን ለፈጠረ፤ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል ዋቃ (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት በዓል ነው።የዘንድሮው በዓል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በስፍራው በተመጠነ የሰው ብዛት ነው እየተከበረ የሚገኘው። በበአሉ ላይ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ብሄር ብሄረሠቦችም ተሣታፊ ሆነዋል

Read 10 times Last modified on Maandag, 05 Oktober 2020 07:03