open

የሱዳን ካርቱም እህት ከተማ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር/የሱዳን ካርቱም እህት ከተማ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

የሱዳን ካርቱም እህት ከተማ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡

የሱዳን ካርቱም እህት ከተማ ከፍተኛ የሉዑካን ቡድን አባላት ከሀምሌ 26 እስከ 29 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ የአዲስ አበባ እህት ከተማ በበሆነቸው የካርቱም ከተማ ገዥ በጀነራል አብደልራሂም መሀመድ ሁሴን የሚመራ የሱዳን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ ጋር ስለ ከተማዋ የግብር አሰባሰብና የኢንቨስትመንት አማራጮች በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በገለፃው ወቅትም ለውጪ ኢንቨስትመንት ክፍት የሆኑ እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ የተፈቀዱ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ በሶስት ቀን ቆይታቸውም የቤቶች ልማትን፣ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂን ፣የኢንዱስትሪ ፓርክን፣ የቴክኒክና ሙያን የስራ እንቅስቃሴ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የካርቱም ከተማ እ.አ.አ. በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ እህት ከተማ ጋር በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በባህል ልውውጥ፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በሌሎችም ዘርፎች አብረው ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው የሚታወስ ነው፡፡

Read 1857 times