open

በከተማዋ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ከ400 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሴፍትኔት ፕሮግራም ተግባራዊ ሊደረግ ነው

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት/በከተማዋ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ከ400 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሴፍትኔት ፕሮግራም ተግባራዊ ሊደረግ ነው

በከተማዋ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ከ400 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የሴፍትኔት ፕሮግራም ተግባራዊ ሊደረግ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ 2009 በጀት ዓመት የሚተገበረው የከተማ የምግብ ዋስትና ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት፣በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ 400 ሺህ በላይ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ  ሀምሌ 29 ቀን 2008 . በከተማ አስተዳደሩ አይሲቲ አዳራሽ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው እንደገለጹት፥ በመርሃ ግብሩ 66 ሺህ በላይ ረዳትና ጧሪ የሌላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ቀጥታ ድጋፍ ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

መዲናዋን ጨምሮ 11 ከተሞች ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ በሚተገበረው የመጀመሪያው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም 600 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

አቶ ኤፍሬም አክለውም ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በከተማዋ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና በማህበራዊ ችግሮች የተጎዱ የህረተሰብ ክፍሎችን  ለመገደገፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ፕሮጀክት /ቤት እንዲቋቋም በካቢኔ መጽደቁንና ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ከዓለም ባንክ መገኘቱን እንዲሁም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እየተጠናቀቁ  መሆኑን ገልፀዋል።

ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተውጣጥቶ የተቋቋመው የከተሞች የምግብ ዋስትና እና የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት በመርሃ ግብሩ የሚሳተፉ አካላትን የመለየቱን ስራ የሚያከናወን ይሆናል።
በቀጣዮቹ አምስት አመታት ለሚተገበረው የመጀመሪያው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም 450 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያስፈልጋል። ለዚህም ከአለም ባንክ 350 ሚሊየን ዶላር ብድር የተገኘ ሲሆን ቀሪው 100 ሚሊየን ዶላር ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፈን ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የአስር  ዓመት ፕሮግራም መሆኑንና የመጀመሪያው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም ሲጠናቀቅም ሁለተኛው ዙር የሚቀጥል መሆኑን ከመግለጫው ለመረዳት ተችሏል።

መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ በምትሰለፍበት ጊዜ በከተሞች ያለውን 22 በመቶ የሆኑ እና ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ሰዎች ካሉበት ደረጃ ከፍ ብለው በምግብ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያስችል እንደሚሆን ይጠበቃል።

በመርሃ ግብሩ የሚካተቱ አረጋውያን፣ የአእምሮ ሁሙማን፣ ወጣቶች እና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ሴተኛ አዳሪዎች እና የደሃ ደሃ ዜጎችን የመለየት ስራ በቅርቡ ይጀመራል  በማለት አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በከተማዋ በልማት ምክንያት በተለያዩ ጊዚያት የሚነሱ አርሶ አደሮችን ለማህበራዊ ችግሮች እንዳይጋለጡና ዘላቂ ልማት እንዲያረጋግጡ እገዛ የሚያደርግ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ፕሮጀክት /ቤት መቋቋሙን ከኃላፊው ገለፃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2036 times Last modified on Maandag, 08 Augustus 2016 12:36