open

አዲስ አበባ ከቹንቹን እህት ከተማ በርካታ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ላይ መሆኗ ተገለፀ (አዲስ አበባ፣ከንቲባ ጽ/ቤት)፣

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ቱሪዝም/አዲስ አበባ ከቹንቹን እህት ከተማ በርካታ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ላይ መሆኗ ተገለፀ (አዲስ አበባ፣ከንቲባ ጽ/ቤት)፣

አዲስ አበባ ከቹንቹን እህት ከተማ በርካታ ተሞክሮዎችን በመቅሰም ላይ መሆኗ ተገለፀ (አዲስ አበባ፣ከንቲባ ጽ/ቤት)፣

በቹንቹን   ከተማ  የማህበራዊ  ጉዳይ  ቢሮ  ኃላፊ  ዮን - ገም- ዬዎን  የተመራ  የልዑካን  ቡድን  ግንቦት  7  ቀን 2009  ዓ.ም.  በአዲስ  አበባ ከተማ  አስተዳደር  ተገኝቶ  ውይይት  አካሂዷል፡፡

በዚህ  ወቅት  የከተማ  አስተዳደሩን  በመወከል  ልዑካኑን  የተቀበሉት  የአዲስ  አበባ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት  ቢሮ  ኃላፊ  አቶ  ፎኤኖ  ፎላ ፣ የሁለቱ  ከተሞች   እህትማማችነት  የጠነከረ  መሆኑን  በመጠቆም ፤ ለዚህ  ደግሞ  መሰረቱ  ኢትዮጵያዊያን  አባቶች  በቃኘው  ሻለቃ  አማካይነት  ከስልሳ  ስድስት  ዓመታት  በፊት  ለኮሪያ  ነፃነት  ያደረጉት  አስተዋጾኦ  እንደሆነ  አስታውሰዋል፡፡

የልዑካኑ  መሪ  ዮን - ገም - ዬዎን  በበኩላቸው፣  የሁለቱን  ከተሞች  ግንኙነት  የሚያጠናክሩ  በርካታ  ፕሮጀክቶች  መኖራቸውንና  በቆይታቸውም  ጉብኝቶች  ያሏቸው  መሆኑን  ተናግረዋል፡፡ መልዕክተኛዋ  ከከተማቸው  ከንቲባ  የተላከውን  5 ሺህ  ዶላር  ለቆሼ ተጎጂዎች  እንዲሰጥም  አበርክተዋል፡፡

የሚመለከታቸው የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች  በተገኙበት በዚህ  ውይይት  ላይ  የቹንቹን  ከተማ  ህፃናትና  ታዳጊ ወጣቶችን   በተመለከተ  በትምህርት  ቤትና ከዚያ  መልስ  ለተማሪዎቻቸው  የሚያደርጉላቸውን  ድጋፍና  ክትትል  በተመለከተ የልዑካን ቡድኑ ዓባል በሆኑት በኩዎን-ሃን-ና ገለፃ  ቀርቧል፡፡ በዚህም  በከተማዋ በተጠቀሰው እድሜ ክልል የሚገኙ ድጋፉ የሚደረግላቸው ተማሪዎች በእንግሊዝኛ  ቋንቋና በሒሳብ  ትምህርቶች  ላይ የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጣቸውና  ደረጃውን  የጠበቀ  የቤተ - መፅሐፍት  አገልግሎቶችን ጭምር  እንደሚያገኙም  ተመልክቷል፡፡

 

የአዲስ  አበባ  ከተማ  አስተዳደርም  በቹንቹንና  በሌሎችም  ከተሞች  የሥራ  ጉብኝት  ካከናወነ  በኃላ  ተሞክሮችን  በመቀመር ፤ መረጃዎችን  አደራጅቶ   መያዙን፣  በአዲስ  አበባ  በኩል  የተዘጋጀውን  ገለፃ  ያቀረቡት  የአዲስ  አበባ  የአደረጃጀትና  መዋቅር ጥናት  ፕሮጀክት  ጽ/ቤት  ኃላፊ  አቶ  ሰይፈ  ፈቃደ  ገልፀዋል፡፡

የእንጦጦ  መዝናኛና  መናፈሻ ፣ የከተማ  ግብርና፣  የፋይናንስ  ግልፀኝነትና  ተጠያቂነት  የመሣሰሉት  ከቹንቹን  የተገኙ  ተሞክሮዎች እንደሆኑና የቹንቹን ከተማ ብሎም መላው  የደቡብ  ኮሪያ  ህዝብ  ለማህበረሰባዊ  አገልግሎቶች ፣ በአረጋዊያንና  አካል ጉዳተኞች የትራንስፖርትና የጤና ክብካቤ ዙሪያ አካቶ  በመስራቱ ረገድ ፣ ለአዲስ  አበባ  በርካታ ልምዶችን ማጋራት  መቻላቸውን አቶ ሰይፈ በገለጻው ወቅት አስረድተዋል፡፡

 

Read 446 times Last modified on Donderdag, 08 Junie 2017 08:52