open

የቀን ገቢግምት ስርዓቱ ሕግና ደንቡን ተከትሎ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ማህበረሰብ/የቀን ገቢግምት ስርዓቱ ሕግና ደንቡን ተከትሎ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

የቀን ገቢግምት ስርዓቱ ሕግና ደንቡን ተከትሎ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት )፡-  በቀን ገቢ ግምት ዙሪያ ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም  በከተማ  አስተዳደሩ ምክር ቤት አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በዚህ ወቅት አቶ አትክልት ገ/እግዚአብሔር የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ ከሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ  ለአንድ ወር ያህል መረጃ ሲሰበሰብ መቆየቱን በማስታወስ፤ እስከ ሐምሌ 30 የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችን ቅሬታ ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም፣ 99.2 % ቅሬታዎች መፈታታቸውን ተናግረዋል፡፡

 

የመረጃ ማጣራት ሥራዉም በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በሁለት እርከኖች  መደራጀቱን የገለፁት የስራ ኃላፊው፣ ቅሬታ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ወደ መደበኛ ቅሬታ ማቅረቢያ ብሎም እስከ መደበኛ ፍርድ ቤት ድረስ ቀርበው ጉዳያቸውን ማስረዳት እንደሚችሉ  አስገንዝበዋል፡፡  

የአዲስ አበባ ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ ፕሮግራም ልማትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ፈቃደ በበኩላቸው፣ ከቀረቡ ቅሬታዎች ውስጥ 30% ያህሉ ማሻሻያ የተደረገባቸው እንደሆነና ይህ ሲባል ግን ምንም ስህተት የለውም ማለት አንዳይደለ አስረድተዋል፡፡

ከአሳታፊነቱ አኳያም የንግዱን ማህበረሰብና ከከተማዋ ም/ቤት ልዩ ልዩ  አደረጃጀቶችና ሕዝቡ ጭምር በዝግጅት፣ በተግባርና በማጠቃለያ ምዕራፎች ማሳተፍ መቻሉን አክለዋል፡፡ አለመግባባቶቹ የተፈጠሩትም ግምቱ ይፋ በሚደረግበት ጊዜ መሆኑን አቶ ያሬድ ጠቁመዋል፡፡

የቀን ገቢ ግምትን ወደ ዘመናዊ ስርዓት ለማስገባትም በደረሰኝ የመሸጥና የመገበያየት ብሎም የሂሳብ መዝገብ አያያዝን አጠናክሮ በመቀጠልና በጥናት በማስደገፍ ማዘመን እንደሚገባ፤ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙ ከልዩ ልዩ ሚዲያዎች የተገኙ ጋዜጠኞች ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ  የሰጡት  ሁለቱ የዘርፉ የሥራ  ኃላፊዎች  አስረድተዋል፡፡

 

Read 858 times