open

አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ውብና ፅዱ ለማድረግ ከሊዮን ልምድ ተወሰደ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት/አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ውብና ፅዱ ለማድረግ ከሊዮን ልምድ ተወሰደ

አዲስ አበባን አረንጓዴ፣ውብና ፅዱ ለማድረግ ከሊዮን ልምድ ተወሰደ

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፈረንሳይዋ  ፅዳት ውበትና ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ከፈረንሳይዋ ሊዮንከመጡ  ልዑካንና  ከሚመለከታቸው የዩንቪርስቲ ምሁራን፣ የቢሮ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የሶስት ቀን ወርክ ሾፕ ከህዳር 19 – 21 ቀን 2010 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል አካሂዷል

 

 በወርክ ሾፑ ላይ ከአስር በላይ  ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የአዲስ አበባን  ፓርኮች፣ ባዶ ቦታዎችና ጎዳናዎችን አረንጓዴ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ  የአዲስ አበባ ፅዳትና ውበት ዘላቂ ማረፊያ  ቢሮ ልዩ ትኩረት የሰጠበት ወርክሾፕ እንደነበረ ተመልክቷል፡፡

 

በቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎችና ፕሮጀክቶች ላይ  በስድስት ቡድን ተመድበው በተጎበኙ ፓርኮችና አረንጓዴ ቦታዎች ጥልቅና መደረግ ያለባቸው ነገሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፣ የሚታዩ ችግሮችንም ለማጥፋትና በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት የባለሙያዎች ሀሳብ ተንሸራሽሮበታል፡፡ በአዲስ አበባ በሚገኙ 16 ወንዞች ዙሪያም አሁን ካለበት መርዛማነትና ቆሻሻነት በማፅዳት ድሮ ለዋናና ለአልባሳት  እጥበት ይጠቅሙ  እንደነበር ለማድረግ አምስት ወንዞች ላይ የሚፅዳትና ተፈጥሮአዊ ቀለማቸውንና ውበታቸውን ይዘው ጥቅም እንዲሰጡ ወደ ወንዞች የሚለቀቁ የመፀዳጃ ቤት ቆሻሻና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ የማድረግ ስራ እየተሰራ  እንደሆነ በቀጣይም 16 ቱንም የአዲስ አበባ  ወንዞች ፅዱ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን  የውበትና ፅዳት  ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ተናግረዋል፡፡

 

አረንጓዴ ተክሎች የሰው ልጅ ትንፋሽ ናቸው እነሱ  ከሌሉ  መተንፈስ እናቆማለን ስለዚህ ለህብረተሰባችን የግንዛቤ ስራ መስራትና ጥበቃ እንዲያደርግ ለራሱ በህይወት  መኖር  እንዲሰራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ከተባበርንና በጋራ ከሰራን የማይቻልና የማንሰራው ነገር የለም ተዓምር መፍጠር  የምንችል ህዝቦች ነን ያሉት ደ/ር ፋንታው ወሰን የወንዶች ገነት  የዩንቨርስቲ ተወካይ  ናቸው፡፡

 

ወ/ሮ  አልማዝ አያይዘውም  በአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን  መሰረት  በተካተቱ የልማት  ቦታዎች ላይ የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ የፅዳትና መናፈሻ እንዲሁም  የወንዞች ዳርቻ ስራ ከመቸውም በበለጠ ትኩረት  ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑንና ባሉት 116 ወረዳዎችም አንድ ፓርክ ለመገንባት በፕላኑ መካተቱ በማስታወስ፣ በመሪ ፕላኑ የተካተቱት በዚህ አመት 50 ፓርኮች ግንባታቸው እንደሚጀመርም ገልፀዋል፡፡ በውበትና ፅዳት ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ በጥቁር አንበሳ አካባቢ ፓርክ በስድስት ወራት ይገነባል የተባለ ቢሆንም በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት  እስካሁን  አለመጠናቀቁ  ችግር ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡

በወርክ ሾፑ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ዘገዬ ቸርነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና ከአርክቴክቸር ህንፃ ግንባታና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ( EIABC ) የአርክቴክቸርና ዲዛይን ክፍል ሀላፊ በዚህ ወርክ ሾፕ የተሳተፉትን ምሁራን፣ ባለሙያዎችና ልምድ ያካፈሉትን የሊዮን ልዑካን አመስግነው በአዲስ አበባ ብሎም በሀገራችን የሚታየውን በስታንዳርድ፣ በፕላን፣በዲዛይንና ባለሙያን ሳያካትት እየተሰራ የነበረ መሆኑን፣ በመግለፅ ከዚህ ወርክ ሾፕ በኋላ ግን ሁሉም ወሬ ማውራቱን ትቶ በተግባር መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ ዶ/ር ዘገዬ አክለውም ለእኛ ዛፍ እንዴት ብርቃችን ይሆናል?እነ ሞባይል፣ኮምፒውተር፣መኪና ሌሎች ብርቅ ይሁኑብን እንጂ በማለት እዚሀ ወርክ ሾፕ የተሳተፋችሁ በሙሉ የሚታዩትን ችግሮች ማለትም የፕላን፣ የስታንዳርድ፣የዲዛይን  የመሳሰሉት በመቅረፍና  በተቀናጀ  ስራ ፓርኮችን፣ በየ መንገዱ ያሉ ክፍት ቦታዎችን እንዲሁም ወንዞችን አረንጓዴ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ የማድረግ ስራ ኃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ብለዋል

Read 1122 times Last modified on Vrydag, 08 Desember 2017 06:25