open

አስተዳደር

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/አስተዳደር

 

የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐቢይ አህመድ የጀግና አቀባበል ስነ ስርዓት ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡:የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው ዕለት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተገኝተው የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን መቀበላቸው ይታወሳል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፕሬስ ሴክሪታሪያት ሓላፊ ወይዘሪት ፌቨን ተሾመ በነገው ዕለት የሚደረገውን የአቀባባል ስነስርዓት አስመልከተው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከኖርዌይ ኦስሎ ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ስነ-ስርዓት ይደረግላቸዋል ብለዋል።

 

 

ከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በፊት የነበረውን ማስተር ፕላን ስራ ላይ ሊያውል ነው እንዲሁም የክፍለ ከተሞች ቁጥር ከአስር ወደ አስራ ሶስት ከፍ እንዲል ሊደረግ ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የስጡት የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደረጀ ፍቃዱ ማስተር ፕላኑ 2008 . በአዲስ አበባ መሪ ፕላን ፕሮጀክት /ቤት የተዘጋጀ ሲሆን ረቂቁ ከህዝብ ባጋጣው ተቃውሞ ውድቅ ተደርጎ ፕሮጀከት /ቤቱም እንዲፈርስ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

መሪ ፕላንን በተመለከተም የከተማ አስተዳደሩ ምንም አይነት አዲስ የከተማ አደረጃጀትም ሆነ ማስተርፕላን የመተግበር እቅድ እንደሌለው አቶ ደረጀ ገልፀዋል፡፡

 

 

/ ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

 

የሸገር ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች የአረንጓዳ ልማት ስራዎች ላይ የቴክኒክ እና የገንዝብ ድጋፍ ማድርግ በስምምነቱ ከተካተቱ ጉዳዩች መካከል አንዱ ነው።

 

በመንገድ ግንባታ ምክኒያት ሊፈርሱ የነበሩ የታላቁ አንዋር መስጅድ አካል የሆኑ ሱቆች አይፈርሱም ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሱቆቹ ዙሪያ ከአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኡለማዎች እና የቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከዚህ ቀደም በህዝበ ሙስሊሙ ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከእምነቱ ተከታዮች እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ በደረሰባቸው ጉዳዮችሱመረ ዙሪያም ተነጋግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት የይዞታ ጥያቄዎችን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሌሎች የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢ/ ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡