open

ቱሪዝም

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ቱሪዝም

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) ሁለቱ እህትማማች ከተሞች የአካል ጉዳተኛና ሌሎች ተማሪዎች በፈጠራ ስራ የታገዘ ትምህርት እንዲያገኙ ከህዳር 12 እስከ 17 ቀን 2010 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በስድስት ቀናት ውይይታቸው የልምድ ልውውጥ  አካሂደዋል፡፡

 

 በዚህ የልምድ ልውውጥ በመጀመሪያው ቀን አዲስ አበባን  በጉዞ የተጎበኘ ሲሆን በተጨማሪም ስለ መረጃ ሁኔታ ሰነድ ቀርቧል፣በሚስተር ክርስቲያን የተዘጋጀውን  በጨዋታ የታገዘ የፈጠራ ስራ ፕሮጀክት ፣ስለ መምህራን ልምድ ከላይቢዚክ  የመጡ መምህራን  ልምዳቸውን በማካፈልና በቪዲዮ (ዶክመንተሪ) የታገዘ የልጆች የፈጠራ ስራም ቀርቧል፡፡

 

የልምድ ልውውጡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ተማሪዎች፣ የተግባረ ዕድ  ተማሪዎች፣ የምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችና የካቶሊክ ቸርች ተማሪዎች ከላይቢዚክ የተገኘውን ልምድ ተግባራዊ በማድረግ በፈጠራና በተግባር የታገዘ ትምህርት እንደሚማሩ ያደርግ ዘንድ ተደርጓል፡፡

 

በተያያዘም የልምድ ልውውጡ በምልክት ቋንቋ ጭምር የተዘጋጀ ሲሆን የአካል ጉዳት ያለባቸውንና ማየት የተሳናቸው ተማሪዎችም በዚህ ፕሮጀክት ታቅፈው ፈጠራቸውንና ክህሎታቸውን በራሳቸው ጥረት የራሳቸውን ዓለም እንዲፈጥሩ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልፆል፡፡

በቹንቹን   ከተማ  የማህበራዊ  ጉዳይ  ቢሮ  ኃላፊ  ዮን - ገም- ዬዎን  የተመራ  የልዑካን  ቡድን  ግንቦት  7  ቀን 2009  ዓ.ም.  በአዲስ  አበባ ከተማ  አስተዳደር  ተገኝቶ  ውይይት  አካሂዷል፡፡

በዚህ  ወቅት  የከተማ  አስተዳደሩን  በመወከል  ልዑካኑን  የተቀበሉት  የአዲስ  አበባ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት  ቢሮ  ኃላፊ  አቶ  ፎኤኖ  ፎላ ፣ የሁለቱ  ከተሞች   እህትማማችነት  የጠነከረ  መሆኑን  በመጠቆም ፤ ለዚህ  ደግሞ  መሰረቱ  ኢትዮጵያዊያን  አባቶች  በቃኘው  ሻለቃ  አማካይነት  ከስልሳ  ስድስት  ዓመታት  በፊት  ለኮሪያ  ነፃነት  ያደረጉት  አስተዋጾኦ  እንደሆነ  አስታውሰዋል፡፡

የልዑካኑ  መሪ  ዮን - ገም - ዬዎን  በበኩላቸው፣  የሁለቱን  ከተሞች  ግንኙነት  የሚያጠናክሩ  በርካታ  ፕሮጀክቶች  መኖራቸውንና  በቆይታቸውም  ጉብኝቶች  ያሏቸው  መሆኑን  ተናግረዋል፡፡ መልዕክተኛዋ  ከከተማቸው  ከንቲባ  የተላከውን  5 ሺህ  ዶላር  ለቆሼ ተጎጂዎች  እንዲሰጥም  አበርክተዋል፡፡

የሚመለከታቸው የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች  በተገኙበት በዚህ  ውይይት  ላይ  የቹንቹን  ከተማ  ህፃናትና  ታዳጊ ወጣቶችን   በተመለከተ  በትምህርት  ቤትና ከዚያ  መልስ  ለተማሪዎቻቸው  የሚያደርጉላቸውን  ድጋፍና  ክትትል  በተመለከተ የልዑካን ቡድኑ ዓባል በሆኑት በኩዎን-ሃን-ና ገለፃ  ቀርቧል፡፡ በዚህም  በከተማዋ በተጠቀሰው እድሜ ክልል የሚገኙ ድጋፉ የሚደረግላቸው ተማሪዎች በእንግሊዝኛ  ቋንቋና በሒሳብ  ትምህርቶች  ላይ የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጣቸውና  ደረጃውን  የጠበቀ  የቤተ - መፅሐፍት  አገልግሎቶችን ጭምር  እንደሚያገኙም  ተመልክቷል፡፡

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፤  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው፣ ከቻይናዋ ፉዡ የመጡ የልዑካን ቡድን አባላትን ታህሳስ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በካቢኔ አዳራሽ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑን የመሩትና የፉዡ ከተማ የኢንዱስትሪ ዞን የቦርድ ሊቀመንበር ሚስተር ዉ ፉቻንግ፣ በሃይድሮ ፓወር፣ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ (ትራንስፎርመር)፣ የኤሌክትሪክ ገመዶችና ተዛማጅ ሥራዎች በተጨማሪም ጨርቃ ጨርቅን በመሳሰሉ በርካታ ዘርፎች ዙሪያ መዋዕለ-ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ጎረቤት አገር ኬንያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ከተሞች ላይ በኢንቨስትመንት ዘርፉ መሰማራታቸውን የገለፁት ሊቀመንበሩ፣ ውጥናቸው በአዲስ አበባና በአጎራባቾችዋ የፉዡ ኢንዱስትሪ ዞንን መገንባት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

 

(አዲስ አበባ፤ ከንቲባ ጽ/ቤት) በሼክ ሳልማን አልጌፍ የተመራ የሳዑዲ አረቢያ ኢንቨስትመንት ቡድን በአዲስ አበባ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት አሳየ፡፡ የኢንቨስትመንት ቡድኑ በቱርክ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በማሌዥያ እና በሳዑዲ አረቢያ በሪል ስቴት ዘርፍ የተሻለ ተሞክሮ ያለው መሆኑና በአፍሪካ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለመሠማራት ማቀዱን ታህሳስ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አዳራሽ በነበረው ውይይት ወቅት አስታውቋል፡፡

በበርካታ ባለሐብቶች ቅንጅት የተቋቋመው የአልጌፍ ኢንቨስትመንት ቡድን ወደ አገራችን መምጣቱ፤ የሁለቱን አገራት የርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር እና ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማሳደግ ረገድ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እምነታቸው መሆኑን የልዑካን ቡድኑ መሪና የአልጌፍ ኢንቨስትመንት ሊቀመንበር ሼክ ሳልማን አልጌፍ  በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ሠላማዊ አገር መሆን፣ የአየር ንብረቷ ምቹነትና የሕዝቦቿ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም ጠንካራ ሰራተኛነት በአገሪቱ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ያሳደረባቸው መሆኑን ሊቀመንበሩ ጨምረው አስረድተዋል፡፡