open

መሰረተ ልማት

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት

 

ሁለት መቶ የእሳት ማጥፊያ ውሃ መቅጃ መሣሪያዎች /fire hydrants /በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ሊተከሉ ነው ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከከተማ እና ከህንፃዎች ዕድገት ጋር ተያይዞ እየሰፋ ከመጣውን የእሳት እና ተያያዥ አደጋዎች ለመቀነስ የእሳት ማጥፊያ የሚያገለግሉ ሁለት መቶ የውሃ መቅጃ መሣሪያዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

 

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ እንደገለፁት የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎቹ(fire hydrants) 8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ ሲሆን፣ ከከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ቦታዎች ይተከላሉ።

 

የእሳት አደጋ ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ውሃ የሚገኘበት ሁኔታ ብቁ ስላልሆነና የከተማው መስፋፋትም የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ያልተተከለባቸው በርካታ አካባቢዎች ስላሉ ቦታዎች ተለይተው እንደሚተከሉ ገልጸዋል፡፡

 

የዓድዋ ማዕከል ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚገነባው ሲሆን በውስጡም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በጥቂቱ
የአድዋ ሙዚየም
2000 ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ

እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት(3) አዳራሾች
የሲኒማ አዳራሽ
ቤተ-መፅሐፍ
የስፖርት ማዘውተርያዎች እና ጂሞች
የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራ
የጌጣጌጥ መደብሮች
የቤተ-ስዕል ማዕከላት
ዘመናዊ የባስ እና የታክሲ ማቆሚያ
600 መቶ መኪና በላይ የመያዝ አቅም ያለው ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ
ካፌዎች እና የምግብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት
ለንባብ አገልግሎት የሚሆኑ የአረንጓዴ ስፍራ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

 

/ ታከለ ኡማ አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤተ-መፅሐፍትን ግንባታ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡

ከወራት በፊት የግንባታ ስምምነቱ የተፈረመው ቤተ-መፅሐፍት

• 38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል
በአንድ ጊዜ 3,500 ሰው የሚያስጠቅም እና በቀን እስከ 10,000 ሰው የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል
ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን ለየብቻ የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ 100 ሰው በላይ የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት የስብሰባ አዳራሾች ይኖሩታል

 

 

/ ታከለ ኡማ የመኪና ማቆሚያ ግንባታውን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

 

10 . ላይ የሚያርፍ እና 1 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችለው ይህ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ አራት ቤዝመንቶች ይኖሩታል፡፡