open

መሰረተ ልማት

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/መሰረተ ልማት

 

/ ታከለ ኡማ የሸጎሌ የአውቶቢስ ዴፖን በዛሬው ዕለት መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡
የሸጎሌ የአውቶቢስ ዴፖ ማዕከል አውቶቢሶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የጋራዥ አገልግሎት የእጥበትና የነዳጅ አቅርቦትን በአንድ ማዕከል የሚያገኙበት ነው፡፡

የሸጎሌ የአውቶቢስ ዴፖ በዋናነት ዘመናዊ የአውቶቢስ ስምሪት ስርዓት መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ ምቹ የአውቶቢስ ማቆሚያ ዘመናዊ የጥገና ማዕከል የአውቶቢሶች ውጪ አካል ቀለም አገልግሎት የአውቶቢስ እጥበት አገልግሎት እና የነዳጅ ማደያ አገልግሎት መስጫን ያካተተ ነው፡፡

የሸጎሌ የአውቶቢስ ዴፖ 52 . ላይ ያረፈ ሲሆን 250- 300 አውቶቢሶችን በተመቻቸ ሁኔታ ከላይ የተጠቀሱ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

 

 

 

 

የከተማ አስተዳደሩ 3000 ዘመናዊ አውቶቢሶችን በቅርቡ በማስገባት በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ይሰራል፡፡"

/ ታከለ ኡማ 400 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎ አስተዳደሩ የገዛቸውን 100 የከተማ አውቶቢሶች ለአንበሳ የከተማ አውቶቢስ አገልግሎት ድርጅት በዛሬው ዕለት አስረክበዋል

(አዲስ አበባ፣ ለከንቲባ ጽ/ቤት) የከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኞች የ2010 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገምና የ2011 የበጀት አመት ዕቅድን በተመለከተ ሐምሌ 19 እና 20 በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ተወያይተዋል፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ አያና  እንዳሉት ለከተማ ለውጥ የከንቲባ ጽ/ቤት ከዝቅተኛ ባለሙያ እስከ ከፍተኛ አመራር በቁርጠኝነት በመነሳት በ2010 ዓ.ም የነበሩ ጉድለቶችንና በበጀት ዓመቱ ያልተሸፈኑ ስራዎችን ወደ 2011 በጀት አመት በማስተላለፍ በዚህ በጀመርነው 2011 በጀት ዓመት ከዘልማዳዊ አሰራር ወጥተን ወደ ዘመናዊና ቀልጣፋ የስራ እንቅስቃሴ በመሸጋገር ውጤታማ ስራ በመስራት በከተማ ያሉ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየተዋረዱ በመፍታት ህብረተሰቡን ማገልገል፣ ብሎም በሁሉም መስክ ውጤታማ ስራ ማስመዝገብ አለብን ብለዋል፡፡