open

ልዮ ልዮ

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/ልዮ ልዮ

 

 

ዛሬ ጠዋት የተካሄደው 6ኛው የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ብዙ ሰው በማሳተፍ በአፍሪካ የመጀመሪያ የማስ ስፖርት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

 

የኢፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከተማዋ በማስ ስፖርት ላስመዘገበችው ድል የእውቅና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ ይህን ድል እንድትቀዳጅ ለሰሩ ላስተባበሩ እና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል፡፡

 

 

/ ታከለ ኡማ መጪው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎች የታብሌት ኮምፒውተር በስጦታ አበርክተዋል፡፡የታብሌት ኮምፒውተሮቹ በከተማዋ ከሚገኙ ባለሃብቶች በስጦታ የተገኘ ነው፡፡

 

በውይይቱ የህገወጥ ግንባታዎችን በተመለከተ የተደረገው ጥናት እና ህግን የማስከበር እርምጃው ማስፈጸሚያ መንገዶች ዙሪያ ትኩረት ተደርጓልየከተማ አስተዳደሩ በተለይም እየተስፋፋ የመጣውን ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ አዋጅ 721/2004 መሠረት በማድረግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን በቅርብ ቀናትም ወደ ትግበራ ይገባል

በቻይና በተካሄደው የዓለም የዩንቨርስቲዎች እግር ኳስ ውድድር አፍሪካን በመወከል ተሳታፊ ለነበረው የኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩንቨርስቲ ልዑካን አቀባበል ተደረገላቸው።ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም የዩንቨርሲቲዎች እግር ኳስ ውድድር አፍሪካን በመወከል ለተሳተፈው የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩንቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የዕውቅናና ምስጋና ፕሮግራም ተካሂዷል