open

Items filtered by date: November 2017

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: November 2017
Items filtered by date: November 2017

 (አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ መድሃኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለ ስልጣን፣ ከጥቅምት 21 እስከ 22 ቀን 2010 ዓ.ም ባለፉት አምስት አመታት በአፈፃፀም በተገኙ ለውጦችና በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ 2መቶ ዘጠና ሶስት ከሚሆኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በጌትፋም ሆቴል የጋራ ውይይት አካሂዷል፡፡

 በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣ ሀገራችን የህዳሴ ጉዞዋን ለማስቀጠል ከምትታወቅበት ተግባር አንዱ የጤናው ዘርፍ መሆኑን በመግለጽ፤ የጤና አገልግሎትና የምግብ መድሀኒት ቁጥጥር ዘርፍም በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2000 ዓ.ም ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በከተማዋም በ2004 ዓ.ም የተቋቋመው የምግብ፣ የመድሃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ባለስልጣን ተስፋ ሰጪ ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 ዜጎችን ለጤና እክልና ለህልፈተ- ህይወት የሚዳርጉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግቦች፣ መጠጦችና መድሃኒቶች ዝውውርን በመቆጣጠር ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ በኩል በመንግስት መዋቅሩ እንዲካተት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ ቁጥጥሩን የጋራ ለማድረግም የጋራ ምክር ቤት ምስረታው ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

 

Published in ልዮ ልዮ

 (አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ  ሰርቪስና ሰው ኃብት ልማት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙት የመንግስት  ሠራተኞች በሪፎርምና ሠራዊት ግንባታ ዙሪያ ከጥቅምት 7-16 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር ለአስር ቀናት ስልጠና ሰጠ፡፡

ከአሰልጣኞቹ መካከል በከንቲባ ጽ/ቤት የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ቡድን ባለሙያ  አቶ እንዳልካቸው ጃጋማ በስልጠናው ወቅት እንደገለፁት፣ ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠቱንና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉት ሁሉም ተቋሟት፣ በክፍላተ- ከተሞችና በወረዳዎች ጭምር በመሰጠት ላይ መሆኑን፤ ዋና አላማውም የፈፃሚውን የመፈፀም አቅም መገንባት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

  

 ባለሙያው አክለውም በከተማው የሚታዩትን አገልግሎት አሰጣጦች በማሻሻል፤ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን በማጥፋት፤ ተገልጋዩን እንደፍላጎቱ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት  እንዲያገኝ ለማድረግ እንደሚያስችል እምነት ተይዞበት ስልጠናው መሰናዳቱን አስገንዝበዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

(በከንቲባ ጽ/ቤት፤ ፕሬስና ህዝብ ግንኙነት ዴስክ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2009 በጀት ዓመት አጠቃላይ ሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ጽ/ቤቶች እና ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም ለክፍለ ከተማ የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤቶች እና ፈፃሚዎች ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ የእውቅና እና የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም አካሄደ፡፡

 

የከንቲባ ጽ/ቤትና ካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አርዓያ በፕሮግራሙ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ላይ እንደገለፁት ውጤታማ የሥራ ምዘና ሥርዓትን መሠረት በማድረግ ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ በመከናወን ላይ የሚገኘው የሽልማት እና እውቅና አሰጣጥ አሰራር በሥራ ክፍሎች እና በፈፃሚዎች መካከል ጤናማ የሥራ የውድድር መንፈስ እንዲጎለብት በማድረግ የጽ/ቤቱን ተቋማዊ አፈፃፀም እያሳደገ መምጣቱን አመልክተዋል፡፡

 

በእውቅና አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የጽ/ቤቱን የ2009 በጀት ምዘና ውጤትና የተገኙ ጠቃሚ ልምዶችን የሚያስቃኝ ሰነድ በሪፎርምና መልካም አስተዳደር ሥራ አመራር ቡድን በኩል ቀርቦ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት አድርገውበታል፡፡

በ2009 በጀት ዓመት በተደረገው ምዘና በከንቲባ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙት 2 ጽ/ቤቶችና 3 ዳይሬክቶሬቶች መካከል የላቀ ውጤት ያስመዘገቡት የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤት፣ የስትራቴጅክ ዕቅድ ዝግጅት ግምገማና ክትትል ዳይሬክቶሬት እና የካቢኔ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ያገኙ ሲሆን፤ ከአስሩም ክፍለ ከተሞች የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽ/ቤቶች መካከል አቃቂ ቃሊቲ፣ ቂርቆስ እና አራዳ ክፍለ ከተሞች በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ የክሪስታል ዋንጫ እና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

 

Published in ልዮ ልዮ

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፡- አስረኛው የሰንደቅ ዓላማ  ቀን ‹‹ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል›› በሚል መሪ ቃል ፣ የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የሚገኙ የልዩ ልዩ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት፤ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ጥቅምት 6 ቀን 2010 ዓ.ም  በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አርዓያ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ለዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንኳን አደረሰን፣ አደረሳችሁ፤ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

 

ምክትል ኃላፊው አያይዘውም፣ ቀደም ባሉት መንግስታት የነበረውን የተዛባ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስተጋብር መሰረቱን በመቀየር፤ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነትን ያረጋገጠው ህገ- መንግስታችን ካካተታቸው ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ውስጥ አንዱ፣ የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ አጠቃላይ ይዘትና ትርጓሜ መሆኑን በማስታወስ፤ በኢፌድሪ አንቀፅ 3 ላይ እንደሰፈረው የሀገራችን ህዝቦችና ሐይማኖቶች በእኩልነት ላይ በመመስረት ተቻችለው መኖራቸውን ማረጋገጥ መቻሉንና ሀገራችን የተያያዘችውን ትልቅ የለውጥ ምዕራፍ መክፈቱን ተናግረዋል፡፡

 

አገሪቱ የጀመረችውን የዲሞክራሲና የእኩልነት ብሎም የህዳሴ ጉዞ ወደፊት ለማስቀጠል ሰላም ዋነኛው መሳሪያ በመሆኑ፤ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣና ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ካለፈው ጊዜ በበለጠ ተነሳሽነትና ትጋት መሥራት እንደሚገባም ምክትል ኃላፊው በአፅንዖት አሳስበዋል፡፡

Published in አስተዳደር