open

Items filtered by date: Desember 2017

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Desember 2017
Items filtered by date: Desember 2017

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች 12ኛውን የህፃናት ቀን ህዳር 22 ቀን 2010ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የምክር ቤት አባላት መሰብሰቢያ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት አክብረዋል፡፡

 

በዓሉ በከንቲባ ጽ/ቤት የሥርዓተ-ፆታ፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ማካተት የስራ ክፍል አዘጋጅነት  ተከብሯል፡፡

 

<< በሴቶችና ህፃናት  ላይ  የሚፈፀመው  ጎጂ  ልማዳዊ  ድርጊቶች  ይቁም !!! በሚል መሪ ቃል  በዓለም  ለ 28ኛ ጊዜ  በሀገራችን  ለ 12ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀን ሁሉም የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የህፃናትን መብት መጠበቅ እንዳለባቸው የጽ/ቤቱ ተወካይና የካቢኔ ጉዳዮች ልዩ ረዳት አቶ ዳዊት ምንዳዬ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት ገልፀዋል፡፡

 

በዕለቱ የህፃናት መብትን አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የሴቶችና ህፃናት ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ማስከበር ባለሙያ አቶ ተሸመ ማሴቦ ሲሆኑ ከተማ አስተዳደሩ በዚህ በያዝነው 2010 በጀት ዓመት ለህፃናት መብት መከበርና በጎዳና የወደቁ ህፃናት ላይ በልዩ ትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ዜጋ የህፃናት መብትን የዘር፣ የሀይማኖት፣የቀለምና የዕድሜ ልዩነት ሳያደርግ በእኩል ፍቅር መጠበቅና መንከባከብ እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ የከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኞችም አስር ህፃናት ከደመወዛቸው በመቁረጥ እየረዱ መሆኑንም ለሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ብሎም ለሀገራችን ህዝብ ጭምር ትልቅ አርያነት ነው በማለት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

 

አቶ ተሾመ ህፃናትን ለመርዳት አምስት ዓይነት የመርጃ መንገዶችን ማለትም ማህበረሰብ አቀፍ፣ ስፖንሰር ሺፕ፣ጉዲፈቻ፣ ዕርዳታ ማሰባሰብና ተቋም ማስገባት ናቸው ብለው በነዚህ መንገዶች መረዳዳት እንዳለብን  አሳስበዋል፡፡ ሰነዱም የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን ያስተናገደ ሲሆን ለጥያቄዎችም የዕለቱ ክብር እንግዳ አቶ  ተሾመ ማሴቦ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል፡፡

Published in ልዮ ልዮ

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፈረንሳይዋ  ፅዳት ውበትና ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ከፈረንሳይዋ ሊዮንከመጡ  ልዑካንና  ከሚመለከታቸው የዩንቪርስቲ ምሁራን፣ የቢሮ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የሶስት ቀን ወርክ ሾፕ ከህዳር 19 – 21 ቀን 2010 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል አካሂዷል

 

 በወርክ ሾፑ ላይ ከአስር በላይ  ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የአዲስ አበባን  ፓርኮች፣ ባዶ ቦታዎችና ጎዳናዎችን አረንጓዴ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ  የአዲስ አበባ ፅዳትና ውበት ዘላቂ ማረፊያ  ቢሮ ልዩ ትኩረት የሰጠበት ወርክሾፕ እንደነበረ ተመልክቷል፡፡

 

በቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎችና ፕሮጀክቶች ላይ  በስድስት ቡድን ተመድበው በተጎበኙ ፓርኮችና አረንጓዴ ቦታዎች ጥልቅና መደረግ ያለባቸው ነገሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፣ የሚታዩ ችግሮችንም ለማጥፋትና በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት የባለሙያዎች ሀሳብ ተንሸራሽሮበታል፡፡ በአዲስ አበባ በሚገኙ 16 ወንዞች ዙሪያም አሁን ካለበት መርዛማነትና ቆሻሻነት በማፅዳት ድሮ ለዋናና ለአልባሳት  እጥበት ይጠቅሙ  እንደነበር ለማድረግ አምስት ወንዞች ላይ የሚፅዳትና ተፈጥሮአዊ ቀለማቸውንና ውበታቸውን ይዘው ጥቅም እንዲሰጡ ወደ ወንዞች የሚለቀቁ የመፀዳጃ ቤት ቆሻሻና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ የማድረግ ስራ እየተሰራ  እንደሆነ በቀጣይም 16 ቱንም የአዲስ አበባ  ወንዞች ፅዱ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን  የውበትና ፅዳት  ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ተናግረዋል፡፡

 

አረንጓዴ ተክሎች የሰው ልጅ ትንፋሽ ናቸው እነሱ  ከሌሉ  መተንፈስ እናቆማለን ስለዚህ ለህብረተሰባችን የግንዛቤ ስራ መስራትና ጥበቃ እንዲያደርግ ለራሱ በህይወት  መኖር  እንዲሰራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ከተባበርንና በጋራ ከሰራን የማይቻልና የማንሰራው ነገር የለም ተዓምር መፍጠር  የምንችል ህዝቦች ነን ያሉት ደ/ር ፋንታው ወሰን የወንዶች ገነት  የዩንቨርስቲ ተወካይ  ናቸው፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በቁጥር 6 የሚሆኑ የኮሪያ ልዑካንን ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም በልማት ዙሪያ በካቢኔ መሰብሰቢያ አዳራሽ አነጋግረዋል፡፡

 

ምክትል ከንቲባው ልዑካኑን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አዲስ አበባ ከኮሪያ ሁለት ከተሞች ማለትም ከሴኡልና ከቹንቹን ጋር የጠበቀ የእህትማማችነት ግንኙነት እንዳላት በመግለጽ፤ የደቡብ ኮሪያ የፓርላማ አባል የሆኑትንና የልዑካን ቡድኑን መሪ ሚስተር ቹንግ ባይጉንግ የዕለቱን አጀንዳ እንዲያቀርቡ ጋብዘዋቸዋል፡፡

 

ሚስተር ቹንግ ባይንጉንግም በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ኢትዮጵያ  ሀገራቸውን ነፃ ለማውጣት ከዛሬ 67 አመታት በፊት ወታደሮቿን  ልካ ነፃ ማውጣቷንና ይህም የደቡብ ኮሪያ ዜጎች ካደረጉት ትግል የላቀ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በኮሪያ የርስ በርስ ጦርነት ወቅት በድህነት ውስጥ መሆናቸውን ተከትሎ፤  እርዳታ የሚቀበሉበት ጊዜ እንደነበርና በአሁኑ ወቅት ግን አደጉ ከተባሉት ሀገራት ተርታ መሰለፍ እንዲችሉ ብሎም በራሳቸው ፖሊስና ስትራቴጂ መመራት እንዲችሉ ኢትዮጵያ ያደረገችላቸውን እርዳታ  ማንም የኮሪያ ዜጋ ሊዘነጋው እንደማይችል አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

 

የዕለቱን አጀንዳም ሲያቀርቡ ቹንቹን ከተማ በአዲስ አበባ ላይ የቡና ሙዝዬም፣ ፋብሪካና ሌሎች አዲስ አበባን ብሎም ሀገሪቱን ተጠቃሚና አገራቸው ከደረሰችበት የኢኮኖሚ ደረጃ እንድትደርስ የበኩላቸውን በመወጣትና ያለባቸውን ውለታ መክፈል ፍላጎት ያላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

‹‹እኛ የቡናና ሻይን እንዲሁም ገንዘብ ሚኒስቴርን አነጋግረን፣ ፕሮጀክታችንን ተቀብለውናል፤ አዲስ አበባም ይህንን ፕሮጀክት ተቀብላን ሥራውን በቅርብ ጊዜ መጀመር  እንፈልጋለን ብለዋል፡፡›› በፕሮጀክቱም ኢትዮጵያ በታሪክ  እንደሚታወቀው  የቡና መገኛ  ሀገር ሆና ሳለ ከቡና የምታገኘው ጥቅም ከዓለም ሀገራት እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ገቢ መሆኑን ያስረዱት ሚስተር ቹንግ፤ ‹‹ እኛ የቡና ልማት  የለንም  ግን ከተለያዩ የዓለም  ሀገራት በማስገባት ትልቅ የውጭ ምንዘሬን ከቡና እናገኛለን፡፡ ስለሆነም ትክክለኛውን የቡና አዘገጃጀትና ባህሉን ጠብቆ ከዓለም ተወዳዳሪ የሆነ የቡና ሙዝዬምና ፋብሪካ መገንባት እንፈልጋለን›› ብለዋል፡፡ የዓለም ሀገራትን የሚያስንቀውን ኦርጅናል ቡና በማቅረብ ዓለም በሙሉ በአካል እየመጣ ኢትዮጵያን ብሎም አዲስ አበባን እንዲጎበኝና ከቱሪዝሙም ተጠቃሚ ለማድረግ ይህንን ፕሮጀክት ይዘው መምጣታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) ሁለተኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት  አምስተኛ ዓመት የስራ ዘመንና አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

 

ምክር ቤቱ በጉባኤው ሁለት አጀንዳዎች ላይ ማለትም በ2010 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር ዕቅድና የደሊቨሪ ዩኒት አሰራር ስርዓት ላይ ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮው የመልካም  አስተዳደር ችግርን በተለየ መልኩ አቅዶ ለምክር ቤቱ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

 

በዕቅዱም በዋናነት በመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ 16፣ በንግድ ቢሮ ሰባት፣ በኢንዱስትሪ ቢሮና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ሦስት፣ በኮንስትራክሽን ቢሮ 13፣ በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ስድስት፣ በቁጠባ ቤቶች አራት፣ በቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስድስት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን 36፣ በአጠቃላይ በስምንቱ ቢሮዎች 91 ችግሮች ተካተውበታል ፡፡

 

በተጨማሪም በመንገዶችና ትራንስፖርት፣ በፍትህ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በደንብ ማስከበር፣ በፖሊስ ኮሚሽን፣ በከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች፣ በወሳኝ ኩነትና ምዝገባ፣ በምግብ መድሐኒትና ጤና እንክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን በተጨማሪም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ቢሮዎች በአስሩም ክፍላተ - ከተሞች 1ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሦስት፣ በ116 ወረዳዎች  1ሺህ ሁለት መቶ አርባ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የለየ ሲሆን ችግሮቹንም ለመፍታት የመፍትሔ አቅጣጫዎችን እንዳስቀመጠላቸው ተመልክቷል፡፡

Published in አስተዳደር

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመሰረተ ልማት ተቋማት በከተማዋ የሚያከኗውኗቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተመለከተ እርስ በርስ በተናበበ ሁናቴ ለመገንባት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም በከንቲባ ጽ/ቤት ICT አዳራሽ ተፈራርመዋል፡፡

 

በስምምነቱ ላይ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ባለሙያና የቴክኒክ ኮሚቴው አባል  አቶ ዘላለም ከተማ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሰነዱም የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት ተቀናጅተው ባለመስራታቸው በቁጥር 18 የሚደርሱ ዋናዋና ችግሮች ለአመታት ሳይፈቱ መቆየታቸው ተመልክቷል፡፡

እነዚህ ችግሮችም ማስተር ፕላኑ መንገድን ብቻ መሰረት ያደረገ መሆኑ፣ በመንገድ ጥናት  ዲዛይን የግዥ ሂደት መሰረተ ልማትን ያማከለ አለመሆኑ፣ የዲዛይን ለውጥ በየጊዜው መደረጉ፣ የጋራ ስራ ዕቅድ አለመኖሩ፣ ለመልሶ ግንባታ በቂ ቦታ አለመዘጋጀቱ፣ የግንባታ ፍቃድ ችግር፣ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ፈቃድ ውጪ መንገድ መቁረጥ፣ መቆፈርና ቆፍረው አለማንሳት በዚህ የተነሳ በአካል ጉዳተኞች፣ በነፍሰጡሮች፣ በህፃናትና አዛውንቶች ላይ የአካልና የጤና ችግር ማስከተሉ፣ በመንገድ ቆረጣ ላይ ደረጃውን የጠበቀ መሳሪያ አለመኖሩና በስታንዳርዱ መሰረት የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በተገቢዉ መንገድ አለማስቀመጥ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ ወቅት በመንገዶች፣ በውሃና ፍሳሽ፣ በኤሌክትሪክና በቴሌኮም መስመሮች ላይ ባለማወቅና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ አንዱ በሌላው ላይ ጉዳት ማስከተል የሚሉት ሰነዱ ያመላከታቸው ዋናዋና ችግሮች ናቸው፡፡

Published in አስተዳደር

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) ሁለቱ እህትማማች ከተሞች የአካል ጉዳተኛና ሌሎች ተማሪዎች በፈጠራ ስራ የታገዘ ትምህርት እንዲያገኙ ከህዳር 12 እስከ 17 ቀን 2010 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በስድስት ቀናት ውይይታቸው የልምድ ልውውጥ  አካሂደዋል፡፡

 

 በዚህ የልምድ ልውውጥ በመጀመሪያው ቀን አዲስ አበባን  በጉዞ የተጎበኘ ሲሆን በተጨማሪም ስለ መረጃ ሁኔታ ሰነድ ቀርቧል፣በሚስተር ክርስቲያን የተዘጋጀውን  በጨዋታ የታገዘ የፈጠራ ስራ ፕሮጀክት ፣ስለ መምህራን ልምድ ከላይቢዚክ  የመጡ መምህራን  ልምዳቸውን በማካፈልና በቪዲዮ (ዶክመንተሪ) የታገዘ የልጆች የፈጠራ ስራም ቀርቧል፡፡

 

የልምድ ልውውጡ በአዲስ አበባ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ተማሪዎች፣ የተግባረ ዕድ  ተማሪዎች፣ የምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችና የካቶሊክ ቸርች ተማሪዎች ከላይቢዚክ የተገኘውን ልምድ ተግባራዊ በማድረግ በፈጠራና በተግባር የታገዘ ትምህርት እንደሚማሩ ያደርግ ዘንድ ተደርጓል፡፡

 

በተያያዘም የልምድ ልውውጡ በምልክት ቋንቋ ጭምር የተዘጋጀ ሲሆን የአካል ጉዳት ያለባቸውንና ማየት የተሳናቸው ተማሪዎችም በዚህ ፕሮጀክት ታቅፈው ፈጠራቸውንና ክህሎታቸውን በራሳቸው ጥረት የራሳቸውን ዓለም እንዲፈጥሩ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልፆል፡፡

Published in ቱሪዝም

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ከንቲባ ጽ/ቤት ከ300መቶ በላይ ለሚሆኑ ተሿሚዎችና ሰራተኞች በሀሰተኛ ማስረጃ መመሪያ ዙሪያ ህዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የምክር ቤት አባላት መሰብሰቢያ አዳራሽ የአንድ ቀን ውይይቱን አካሄዷል፡፡

 

በውይይቱ ላይ የሐሰተኛ የትም/ት ማስረጃና የሙያ ብቃትን አስመልክቶ የመመሪያውን ሰነድ በአቶ ዳዊት ምንዳዬ የካቢኔ ጉዳዮች ልዩ ረዳት  ቀርቦ ተወያዮችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ሰጥተውበታል፡፡

 

በሰነዱ የሐሰተኛ ማስረጃና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው አካላት በ30 ቀናት ውስጥ ራሳቸውን በማጋለጥና በመጠቆም ምህረት ማግኘት እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ይህን ተግባራዊ የማያደርጉ ግን ቅጣታቸው የከፋ እንደሚሆን ተገልፆል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የከንቲባ ጽ/ቤት የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ አፈታት መስተናገጃ ዳይሬክቶሬት ምክትል ሀላፊ የሆኑት  ወ/ሮ ሀይማኖት ወልደ ገብርኤል  መንግስት  ምህረት ማድረጉ ትልቅና አባትነቱን የሚያሳይ ነው ነገር ግን 30 ቀናት በጣም ብዙ ነው ሰነድ ለማሸሽና ለማጥፋት አመቺ ጊዜ ነው ጊዜው ቢያጥርና በህመም፣በረፍት፣ በወሊድና በስራ ምክንያት የሌሉትም በተለየ ሁኔታ ሲመለሱ ቢታዩ መልካም ነው ብለዋል፡፡

Published in ልዮ ልዮ