open

Items filtered by date: Julie 2017

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Julie 2017
Items filtered by date: Julie 2017

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከጣሊያንና ከፈረንሳይ የዕድገት ማህበር ኤጀንሲ ጋር ለንፁህ ውሃ አቅርቦትና  ለፅዳት የሚውል የ7መቶ ሺህ ዩሮ (18 ሚሊዮን ብር) ገደማ ስምምነት ሐምሌ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በከንቲባ ጽ/ቤት የካቢኔ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራርሟል፡፡

በስምምነቱ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ  ምክትል ኀላፊ አቶ ኀይለስላሴ ፍስሃ፣ የጣሊያንና የፈረንሳይ የእድገት ማህበር ኤጀንሲ እርዳታ፣ በአዲስ አበባ መካኒሳ እና ላፍቶ አካባቢ በተመረጡ አራት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ ለተማሪዎች ንፁህ ውሃ በማቅረብ  ንፅህናቸዉን ለመጠበቅ እንደሚያስችላቸዉ ተናግረዋል፡፡

 

ከአሁን በፊት ተፈጥሮ የነበረውን የአተትና ሌሎች በትላትል ሳቢያ የሚመጡ ተላላፊ በሽታዎችን ጭምር ለመከላከል እንደሚያስችል የተናገሩት ምክትል የቢሮ ኀላፊዉ፣ በቀጣይ 2010 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራው እንደሚገቡ ገልፀዋል፡፡ ከዋሽ ፕሮግራም ጋር የሚሰራው  ሥራ በየትምህርት ቤቱ መፀዳጃ ቤት የሚሰራባቸው ዝቅተኛ  ገቢ ያላቸው የተማሪ ቤተሰቦችን ማዕከል አድርጎ፤ ትምህርት ቤቶቹ እንደተመረጡ በማስገንዘብ፤ ይህንን እርዳታ ላደረጉት የጣሊያንና ፈረንሳይ ተወካዮች ምስጋናቸዉ ከፍተኛ እንደሆነ ምክትል የቢሮ ኀላፊዉ ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

Published in ልዮ ልዮ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት )፡-  በቀን ገቢ ግምት ዙሪያ ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም  በከተማ  አስተዳደሩ ምክር ቤት አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በዚህ ወቅት አቶ አትክልት ገ/እግዚአብሔር የአዲስ አበባ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ፣ ከሚያዝያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ  ለአንድ ወር ያህል መረጃ ሲሰበሰብ መቆየቱን በማስታወስ፤ እስከ ሐምሌ 30 የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችን ቅሬታ ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም፣ 99.2 % ቅሬታዎች መፈታታቸውን ተናግረዋል፡፡

 

የመረጃ ማጣራት ሥራዉም በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በሁለት እርከኖች  መደራጀቱን የገለፁት የስራ ኃላፊው፣ ቅሬታ ያለባቸው ግብር ከፋዮች ወደ መደበኛ ቅሬታ ማቅረቢያ ብሎም እስከ መደበኛ ፍርድ ቤት ድረስ ቀርበው ጉዳያቸውን ማስረዳት እንደሚችሉ  አስገንዝበዋል፡፡  

Published in ማህበረሰብ