open

Items filtered by date: Augustus 2017

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Augustus 2017
Items filtered by date: Augustus 2017

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፣  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የ2009 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ሐምሌ 10 ቀን 2009 ዓ.ም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በምክር ቤት መሰብሰቢያ  አዳራሽ ገምግሟል፡፡

በግምገማው ወቅት የአራት ዳይሬክቶሬቶችንና የሶስት ጽ/ቤቶችን ሪፖርት የገመገመ ሲሆን ከሪፖርቶቹ ውስጥ የተወሰኑት በአቀራረብና በአዘገጃጀታቸው መልካም መሆናቸውን ነገር ግን የተሰጠው የሪፖርት  ማቅረቢያ  ሰዓት ማጠሩ፣ ሪፖርቱን  ሙሉ በሙሉ  ለመገምገም በቂ አለመሆኑንና  አዲስ  አበባን እንደ ስፋቷና የስራዎቿ ብዛት በአንድ ቀን ቀርቶ በአራትና በአምስት ቀናት መገምገም በቂ እንዳልሆነ ተገልጿል፡፡

 

በሪፖርት ግምገማው የተለያዩ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን  ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ቅሬታዎች ሙሉ በሙሉ ባልተፈቱበት፤ አፈፃፀማችን ጥሩ ነው ለማለት እንደማያስደፍር፤ ከተማችን ቆሻሻና ሽታ የበዛባት ሆና ሳለ አዲስ አበባ  ለማለት እንደሚከብድ፤ የግዥ ስርዓቱ ጥራት ያለው ዕቃ ለሰራተኛው እንደማያቀርብ የሚሉና ሌሎችም የመልካም  አስተዳደር ችግሮች በውይይቱ ተነስተዋል፡፡

Published in ልዮ ልዮ

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የሶማሊያ የሀገር ውስጥና የፌደራል እርቀሰላም ሚኒስቴር ቋሚ ጸሐፊ አብዱላሂ መሀሙድ ሐሰን የተመራ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አዳራሽ በመገኘት ከክቡር ከንቲባ ድሪባ ኩማና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ለልዑካን ቡድኑ ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንደገለፁት፣ የላቀ አክብሮት በሚሰጣቸው የሶማሊያ ሪፐብሊክ መንግስት ሚንስትሮችና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራው የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገኝቶ፤  የከተማዋን ልምድ ለመቅሰም ያሳየውን ፍላጎት አድንቀዋል፡፡

 

የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ሰፊ ድንበር የሚዋሰኑና ለረጅም ዘመናት የዘለቀ ጉርብትናን ያዳበሩ ህዝቦች ያሏቸው ሀገራት መሆናቸውን የጠቀሱት ከንቲባ ድሪባ፣ በተለይም አትዮጵያ ለሶማሊያ ሠላምና ደህንነት መከበር እያበረከተች ያለችው ሚና የላቀ መሆኑን በማስታወስ፤ ሶማሊያን የተረጋገጋች የከተማ ልማት ማዕከል ለማድረግ የሶማሊያ ሪፐብሊክ መንግስት በሚያደርገው ጥረት አዲስ አበባ ልምዷን በማካፈል ድጋፍ እንደምታደርግ ከንቲባው ጨምረው አስረድተዋል፡፡

Published in አስተዳደር

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በከተማዋ ውስጥ  የቤት ለቤት የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ሥራ የተሰማሩ ማህበራትን አሰራር ለማዘመን የሚያግዙ 54 የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ተሸከርካሪዎችን ሐምሌ 27 ቀን 2009 ዓ.ም ለፅዳት ማህበራት አስረከቡ፡፡

ክቡር ከንቲባ ድሪባ ኩማ በቁልፍ ርክክቡ ስነ-ሥርዓት ላይ ባሰሙት ንግግር፣ የከተማዋን ፅዳት ለመጠበቅ በሚደረገው ርብርብ አዲስ ካፒታል፣ በላይ አብ ሞተርስና በተለይ የፅዳት ማህበራት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በጉልበታቸውና በላባቸው እያደረጉ ላለው አስተዋፅኦ ምስጋናቸው ላቅ ያለ መሆኑንና በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ የማይለያቸው መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ     ኃይሌ ፍስሃ በበኩላቸው በቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ሥራ ለተሰማሩት ማህበራት የተላለፉት ተሸከርካሪዎች በከተማዋ እየተሰራበት ያለውን የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የሚያዘምን ከመሆኑም ባሻገር የፅዳት ሠራተኞችን ጉልበትና ጊዜ በመቆጠብ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት አረንጓዴ ጎርፍ የፅዳት ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ሐየሎም አይተነው በቁልፍ ርክክብ ወቅት እንደገለፀው፣ የደረቅ ቆሻሻ ማጓጓዣ መኪናው የፅዳት አገልግሎቱን የሚያቀላጥፍ ከመሆኑም በላይ ለማህበራቱ አባላት ሥራ ምቹ እንደሚሆን ያለውን እምነት ገልጿል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ ስራ አጥ ወገኖች ስራን ባለመናቅና አድምቶ በመስራት ለውጤታማነት መብቃት እንደሚችሉ የራሱን ተሞክሮ የጠቀሰው ወጣት ሐየሎም፤ በ181 ብር የወር ደመወዝ ስራውን መጀመሩንና በአሁኑ ወቅት በወር ከ3ሺህ እስከ 5ሺህ ብር ድረስ ደመወዝ እንደሚያገኝና ዘርፉ ጥሩ መተዳደሪያ እንደተፈጠረለት አስረድቷል፡፡

 

የከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ መኪናዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከቀረጥ ነፃ ያስገባ ሲሆን፤ የአንዱ መኪና ዋጋ 392 ሺህ ብር መሆኑን እና ማህበራቱ ከተሸከርካሪው አጠቃላይ ዋጋ 20 በመቶ ያህሉን መቆጠብ ቀሪውን 80 በመቶ በሂደት እንዲከፍሉ ብድር መመቻቸቱ ታውቋል፡፡ 

Published in ማህበረሰብ