open

Items filtered by date: Mei 2018

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Mei 2018
Items filtered by date: Mei 2018

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) 77ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል በዓል የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት፤ በአራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትና የአርበኞች የበላይ ጠባቂ  ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)  በንግግራቸው ወቅት፣ አያቶቻቻንና አባቶቻችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የመጣውን የዘመኑን ኃይል ወራሪውን ፋሺስት የኢጣሊያ ሠራዊት በጦር፣  በጎራዴና በጋሻ በአድዋ አውደ-ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን በማሸነፍ፤ ሀገራቸውን ከቅኝ ግዛት ለመታደግ ችለው፤ ለመላው የአለም ጥቁር ህዝብ ምሳሌ  አድርገውናል ሲሉ ዘክረዋቸዋል፡፡

 

ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም  የምናከብረው  የድል ቀን ጣልያን በድጋሚ በአድዋ የደረሰበትን አሳፋሪ ሽንፈት ለመበቀል፣ ከ45 ዓመታት በኋላ  ሀገራችንን ለመውረር  በመጣበት ወቅት፣ የወቅቱ ኢትዮጵያዉያን  አርበኞች አያቶቻችን፣ አባቶቻቸው እና እናቶቻቸው በአድዋ የፈጸሙትን ገድል በማስታወስ እና ኢትዮጵያውያን በጀግንነት በሀገር ጉዳይ የማንደራደር  በመሆናችን ምንም እንኳን በዘመናዊ መሳሪያ እራሱን  አስታጥቆና ከአድዋው  ጦርነት ተምሮ ወታደሩን የበለጠ  አሰልጥኖ  ቢመጣም፤ በየዱር ገደሉና በየጫካው ፋታ በማሳጣት፣ ለአምስት  አመታት በአርበኝነት የአድዋውን ድል የደገሙበት በመሆኑ ታላቅ ክብር ለአርበኞቻችን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡ 

Published in አስተዳደር

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) በከንቲባ ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የስርዓተ ፆታና ወጣቶች ማካተት የስራ ሂደት በኤች አይ ቪ ኤድስ ፈንድ  መመሪያ ዙሪያ ሚያዝያ 24 ቀን 2010 ዓ.ም  ለጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናውን የሰጡት በአዲስ አበባ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የማህበረሰብ ንቅናቄና የሜንስትሪሚንግ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ ደንቡ ሲሆኑ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፈንድ በኤች አይ ቪ ኤድስ ለተጠቁና ወላጃቸውን ላጡ ቤተሰቦች የህክምና ድጋፍና እንክብካቤ ለማድረግ የተቋማት ሰራተኞች በገንዘብ፣ በአይነትና በጉልበት በፈቃደኝነት የሚያደርጉት አስተዋፆኦ መሆኑን፣ መዋጮውንም በተመለከተ ከ0.5 በመቶ አንስቶ በፍላጎት በማዋጣት ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ ሰራተኞች፣ ወላጆቻቸውን በቫይረሱ ላጡ ህፃናትና ለአሳዳጊዎቻቸው ለኢኮኖሚያዊና ለማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ፍጆታ እንዲደግፋቸው የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

ይህን ተግባር የሚያከናወኑ ከየመስሪያ ቤቱ ተመርጠው በነፃ አገልግሎት የሚሰጡ የሜንስትሪሚንግ ግብረ-ኃይሎች እንዳሉም አስገንዝበዋል፡፡ የሜንስትሪሚንግ መርሆዎችን አስመልክቶም መድልዎ አልባነት፣ የፆታ እኩልነት፣ ጤናማ የስራ አካባቢ፣ ማህበራዊ ውይይት፣ ምርመራ ማድረግ፣ ሚስጥራዊነትና በቫይረሱ ለተያዙ ሰራተኞች የስራ ዋስትና መስጠት መሆናቸው በቀረበው የስልጠና ሰነድ ላይ ተመልክቷል፡፡

 

በአዲስ አበባ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ህፃናት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃም ከ127 ሺህ በላይ ህፃናት፣ በኤች አይ ቪ ኤድስ ምክንያት ወላጆቻቸውን በማጣታቸው፤ ለመማርና መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንዳቃታቸውና እንደውም  በምግብ እጦት ምክንያት በትምህርት ቤት እየተማሩ አዙሯቸው የሚወድቁ ህፃናት ጭምር እንዳሉና በቀን አንዴ እንኳን የማይመገቡ መኖራቸው በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

Published in ልዮ ልዮ