open

Items filtered by date: Julie 2018

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Julie 2018
Items filtered by date: Julie 2018

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለከተማዋ አመራሮች ሐምሌ 12 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ የሥራ መመርያ ሰጥተዋል።

 

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በምክትል ከንቲባ ማእረግ ከተሾሙት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ከኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ(ዶ/ር) ጋር በጋራ በመሆን ከከተማ፣ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ተገናኝተው ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅትም ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ(ኢንጂነር) ለአመራሮቹ የሥራ መመርያ አስተላልፈዋል። ምክትል ከንቲባው ባስተላለፉት የሥራ መመርያም የትኛውም አይነት የመንግስት ስብሰባ ከሥራ ሰዓት ውጪ መሆን እንዳለበት አስታውቀዋል።

Published in አስተዳደር

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው፣ 31ኛውን የከተማዋን ከንቲባ ሹመት አጽድቋል፡፡ በከንቲባነት ሹመታቸው ያለፉትን አምስት አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ድሪባ ኩማ የሹመት ጊዜያቸው በማለቁ ኃላፊነታቸውን ለከንቲባ ታከለ ኡማ በንቲ (ኢንጂነር) አስረክበዋል፡፡

 አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፤ የምክር ቤት አባል ባለመሆናቸዉ፣ ለጊዜዉ በምክትል ከንቲባነት ተሰይመዉ የዋና ከንቲባነቱን ሥራ  ያከናዉናሉ፡፡

 በተያያዘም ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በማድረግ ሁለት ሹመቶችንም ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና  ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) በምክትል ከንቲባ አድርጎሾመዋል።

Published in አስተዳደር