open

Items filtered by date: Augustus 2018

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Augustus 2018
Items filtered by date: Augustus 2018

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የክረምት በጐ ቃደኛ ወጣቶችን ሰብስቦ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ አወያይቷል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንዳሉት፣ ወጣቱ በበጐ ፈቃድ አገልግሎቱ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የማይተካ እና ጉልህ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ወጣቱ በሀይማኖታዊ በዓላት የሚያደርገውን አካባቢን የማፅዳት፣ አቅመ ደካሞችን የመርዳት ባህሉን በበዓላት ወቅት ብቻ አከናውኖ ማቆም ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ በማስቀጠል፣ ከተማችንን ከአካባቢ እስከ ወረዳ ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ ብሎም ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በማዳረስ አሁን የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል፡፡ምክትል ከንቲባዋ አክለውም በየአካባቢው የሚገኙ ታዋቂ ሰዎችን፣ አርቲስቶችን፣ ባለ ሀብቶችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን በማስተባበር የተለያዩ የቁሳቁስ እርዳታዎች ያደርጉ ዘንድ እንዲያስተባበሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

Published in አስተዳደር

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ  ነሐሴ 5 ቀን 2010 ዓ.ም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሚድያዎች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫዉ ያነሷቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮችም በቢሮ ደረጃ የተጀመረዉ ሪፎርም አስከ ታችኛዉ መዋቅር  ተግባራዊ እንደሚሆን፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉን የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማት ሥራ እንደሚያከናዉኑ፣ ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ የቤት ልማት ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም ከነበረዉ አሰራር በተለየ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ አዲስ የቤት ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም የነዋሪዎች መታወቂያ ወደ ዲጂታል ካርድ እንደሚቀየር፣ ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡን እያማረረ የሚገኘዉን በተለይ የዉሃን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ለማድረግ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር መግባባት ላይ መደረሱን እና መሬትና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ኦዲት የማድረግ ሥራ በቅርቡ እንደሚጀመር በእለቱ ለተገኙ ጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡

 

 

 

Published in አስተዳደር

 

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ለምክር ቤቱ አቅርበው ያጸደቋቸው የካቢኔ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡


1.
/ አልማዝ አብርሃ ለሴቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊነት
2.
/ ፍሬህይወት ተፈራ ለፍትህ ቢሮ ኃላፊነት
3.
አቶ ጀማሉ ጀምበር ለወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊነት
4.
አቶ ሺሰማህ  /ስላሴ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊነት
5.
ፍሬህይወት /ህይወት(ዶ/ር) ለፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ላፊነት
6.
አቶ አሰፋ ዮሐንስ ለቴክኒክና ሙያ ቢሮ ላፊነት
7.
ኢንጂነር ኤርምያስ ኪሮስ ለኢንደስትሪ ቢሮ ላፊነት
8.
አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ለንግድ ቢሮ ላፊነት
9.
አቶ ፎኢኖ ፎላ ለፋይናንስ ቢሮ ላፊነት
10.
ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ለኮንስትራክሽን ቢሮ ላፊነት
11.
ኢንጂነር ሽመለስ እሸቱ ለመሬት ማኔጅመንት ቢሮ ላፊነት
12.
አቶ ደረጀ ፈቃዱ ለፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነርነት
13.
አቶ ዘውዱ ቀፀላ ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ላፊነት
14.
/ ዮሐንስ ጫላ ለጤና ቢሮ ላፊነት

15.አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ ኃላፊነት
16.
ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠውቤቶች ልማት ቢሮ ላፊነት
17.
ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ለባህልና ቱሪዝም ቢሮ ላፊነት

18.ታቦር ገ/መድህን (ዶ/ር) ለትምህርት ቢሮ ኃላፊነት

19. ኢንጂነር ዘሪሁን አባተን ለዉሃ ቢሮ ኢንጂነር፣

20. ኢንጂነር አወቀ ኃ/ማርያምን ለሥራ አስኪያጅነት፣

 21. አቶ አዳሙ አያናን ለካቢኔ ጉዳዮችና ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊነት፣

22. አቶ ተስፋዬ በልጅጌን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የህዝብ ግንኙነት ዋና አማከሪነት፣

23. ኢንጂነር አለም አሰፋን ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅነት

ወ/ሮ አበበች ነጋሽን በአፈ-ጉባኤነት  ሾሟል፡፡

Published in አስተዳደር

(አዲስ አበባ፣ ለከንቲባ ጽ/ቤት) የከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኞች የ2010 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምን በመገምገምና የ2011 የበጀት አመት ዕቅድን በተመለከተ ሐምሌ 19 እና 20 በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ተወያይተዋል፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ አያና  እንዳሉት ለከተማ ለውጥ የከንቲባ ጽ/ቤት ከዝቅተኛ ባለሙያ እስከ ከፍተኛ አመራር በቁርጠኝነት በመነሳት በ2010 ዓ.ም የነበሩ ጉድለቶችንና በበጀት ዓመቱ ያልተሸፈኑ ስራዎችን ወደ 2011 በጀት አመት በማስተላለፍ በዚህ በጀመርነው 2011 በጀት ዓመት ከዘልማዳዊ አሰራር ወጥተን ወደ ዘመናዊና ቀልጣፋ የስራ እንቅስቃሴ በመሸጋገር ውጤታማ ስራ በመስራት በከተማ ያሉ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየተዋረዱ በመፍታት ህብረተሰቡን ማገልገል፣ ብሎም በሁሉም መስክ ውጤታማ ስራ ማስመዝገብ አለብን ብለዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር የገዛቸዉን 307 የሚሆኑ ተሸከርካሪዎች ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓ.ምለአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ በሚሊንዬም አዳራሽ ርክክብ ፈፅሟል፡፡

በርክክቡ ወቅት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከነቲባ ዶክትር ኢንጂኔር  ሰሎሞን ኪዳኔ እንዳሉት በከፍተኛ ሁኔታ የሰዉ ሕይወትና ንብረት ጥፋት የሚያስከትለዉ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ከተማ አስተዳደሩ ብዙ ስራዎችን እየሰራ አንደሚገኝና የትራፊክ ፖሊሶች በፍትነትና በቅልጥፍና በየትኛዉም አካባቢ ተደራሽነታቸዉን ለማስፋት 275 ሞተር ብስክሌቶች፣ 26 ሚኒባሶች፣ አራት ፒክ አፖች፣ ሁለት አምቡላንሶች ግዥ ፈጽሞ በዛሬዉ እለት አስረክቧል ብለዋል፡፡ ምክትል ከንቲባዉ አያዘዉም የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳሮችን፣ ከመጠን በላይ ጠጥቶ መሽከርከር የትንፋሽ መመርመሪያዎችን፣ አፕሊኬሽን የተሞላላቸዉ  ሞባይሎችንም በጭለቱ አስረክቧል ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዉ በመልዕክታቸዉ መሳሪያዎቹንና ተሽከርካሪዎቹን ገዝቶ ማስረከብ ብቻዉን ለዉት እንዳልሆነና የትራፊክ ፖሊሶች ጥብቅ ዲሲፕሊንና በቂ የክህሎት ስልጠና ታግዘዉ ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት በማገልገል የሰዉ ሕይወት የሚቀጥፈዉን የትራፊክ አደጋ መቀነስ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

Published in ልዮ ልዮ