open

Items filtered by date: Desember 2019

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Desember 2019
Items filtered by date: Desember 2019

 

 

/ ታከለ ኡማ ከፈረንሳይዋ ሊዩን ከተማ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ኬሚልፊልድ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በሊዬን ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ሲሆን በተለያዩ መስኮችም በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።

 

የሸገር ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች የአረንጓዳ ልማት ስራዎች ላይ የቴክኒክ እና የገንዝብ ድጋፍ ማድርግ በስምምነቱ ከተካተቱ ጉዳዩች መካከል አንዱ ነው።

Published in አስተዳደር

 

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራት ክፍለ ከተሞች 132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ሊገነቡ ነው፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ኮሚሽን ኮሚሽነር / አለም አሰፋ እንደገለጹት በከተማዋ የመናፈሻ ፓርኮች ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እየተሰራ ይገኛል፡፡በቅርቡም የከተማው ካቢኔ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህም የከተማዋን አረንጓዴነት ያጠናክራሉ የተባሉ እና ለነዋሪዎቿ የመዝናኛ አማራጭ ያሰፋሉ የተባሉ በአራት ክፍለ ከተሞች በሚገኑ 132 ሄክታር መሬት ላይ የመናፈሻ ፓርኮች ግንባታ ለማካሄድ የመሬት ልየታ ስራ መሰራቱን / አለም አሰፋ ተናግረዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

ሁለት መቶ የእሳት ማጥፊያ ውሃ መቅጃ መሣሪያዎች /fire hydrants /በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ሊተከሉ ነው ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከከተማ እና ከህንፃዎች ዕድገት ጋር ተያይዞ እየሰፋ ከመጣውን የእሳት እና ተያያዥ አደጋዎች ለመቀነስ የእሳት ማጥፊያ የሚያገለግሉ ሁለት መቶ የውሃ መቅጃ መሣሪያዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

 

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ እንደገለፁት የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎቹ(fire hydrants) 8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ ሲሆን፣ ከከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ቦታዎች ይተከላሉ።

 

የእሳት አደጋ ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ውሃ የሚገኘበት ሁኔታ ብቁ ስላልሆነና የከተማው መስፋፋትም የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ያልተተከለባቸው በርካታ አካባቢዎች ስላሉ ቦታዎች ተለይተው እንደሚተከሉ ገልጸዋል፡፡

Published in መሰረተ ልማት

 

በመንገድ ግንባታ ምክኒያት ሊፈርሱ የነበሩ የታላቁ አንዋር መስጅድ አካል የሆኑ ሱቆች አይፈርሱም ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሱቆቹ ዙሪያ ከአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኡለማዎች እና የቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከዚህ ቀደም በህዝበ ሙስሊሙ ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከእምነቱ ተከታዮች እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ በደረሰባቸው ጉዳዮችሱመረ ዙሪያም ተነጋግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት የይዞታ ጥያቄዎችን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሌሎች የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢ/ ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

Published in አስተዳደር

 

 

9ኛው ከተማ አቀፍ የአካል_ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል ነገ ቅዳሜ ህዳር 20 ቀን 2012 . በድምቀት ይጀመራል

"የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎና መሪነት በማጎልበት 2030 የልማት አጀንዳን ውጤታማነት እናረጋግጣለን "በሚል መሪ ቃል በልደታ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት የሚካሄድ መሆኑን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አረጋይ ተናግረዋል፡፡
በሰባት የስፖርት አይነቶች ከአስሩም ክፍለ ከተሞች በሁለቱም ፆታ ከአንድ ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
ስፖርታዊ ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 20 ቀን 2012 . ጀምሮ በልደታ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት ለተከታታይ ስምንት ቀናት በተለያዩ የስፖርት ማዞተሪያ ስፍራዎች ይካሄዳል፡፡

 

Published in ልዮ ልዮ

 

 

 

የኤች. አይ .. ኤድስ ቫይረስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የማህበረሰቡን ተሳትፎ ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ዓለም አቀፍ የኤች አይ ኤዲስ ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይከበራል::

በከተሞች በወረርሽኝ ደረጃ የደረሰውን የኤች አይ ኤድስ ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሀገር ውስጥ ሀብትን እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ ይበልጥ በማሳደግ መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ኤች አይ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ /ቤት አስታወቀ፡፡

 

የጽህፈት ቤቱ ሓላፊ ሲስተር ብርዛፍ ገብሩ 2012 በጀት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በገመገሙበት ወቅት እንደገለጹ ኤች አይ ኤድስ ቫይረስ መልሶ ሊያገረሽ ወደ ማይችልበት ደረጃ ለማምጣት ከመንግስት በተጨማሪ ህብረተሰቡ ተሳትፎውን ሊያጠናክር ይገባል ብለዋል፡፡

Published in ማህበረሰብ

 

የትራፊክ ፍሰትን ከአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ በአዲስ አበባ ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ እንቅስቃሴን ከአንድ ማእከል ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂ ለመተግበር ቅድመ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
አስተዳደሩ በቀጣይ ዓመታት Intelligent Transport System /ITS/ ወደሚባል ቴክኖሎጂ ለመሸጋገር ዕቅድ መያዙን የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ብዙወርቅ ቢሰውር ተናግረዋል።
እያንዳንዱ የመንገድ ላይ እንቅስቃሴ በካሜራ ቴክኖሎጂ የሚታገዝ፣ በእያንዳንዱ ዋና፣ ዋና መንገድ ላይ የትራፊኩን እንቅስቃሴ በአንድ ማዕከል ውስጥ ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በዋና፣ ዋና መንገዶች ላይ በሚተከሉ ካሜራዎች አማካኝነት መረጃዎች ወደ ማእከል በመላክ አንድ ጥፋት ያጠፋ ተሽከርካሪ ምን እንደሠራ እና የተሽከርካሪውን የሰሌዳ ቁጥር በካሜራ የተቀረጹ ምስሎች ወደ ማእከል በመላክ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።


Published in ማህበረሰብ

 

ሁለተኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ህዳር 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም አስቻለው እንደገለጹት ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል፡፡የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በሁሉም ተቋማት የእቅድ ግምገማ አድርገው ጥንካሬ እና ድክመታቸውን በእቅዳቸው ሊሰሩ የሚችሉ ግቦች ላይ ተፈራርመው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Published in አስተዳደር