open

Items filtered by date: Oktober 2020

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና/Items filtered by date: Oktober 2020
Items filtered by date: Oktober 2020

 

8 አመት 1ኛው መደበኛ ጉባኤ የአስፈጻሚ አካላት 2013 በጀት ዓመት የሶስት ወራት እቅድ አፈጻጸም እንደሚገመግም የምክር ቤቱ የፕሬስና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስዓለም እንቻለው ገልጸዋል፡፡በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን እንደገና የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማካሄድ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያስተላልፍ አቶ አዲስዓለም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪ በምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ አቅራቢነት ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚሰጡም ጠቁመዋል፡

Published in አስተዳደር

 

"የትራንስፖርት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከአውቶብስ አቅርቦት በተጨማሪ ዘመናዊ የትራንስፖርት የመሰረተ ልማት ስርዓት እንዲዘረጋ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው" ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኪራይ ወደ ስምሪት የሚገቡ 560 አውቶብሶች ስራ አስጀምረዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እንደገለጹት በከተማዋ የሚታየው የትራንስፖርት ችግር በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡የትራንስፖርት ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ለመፍታት በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ የጋር ትብብር 560 አውቶብሶችን በኪራይ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ መወሰኑን / አዳነች ተናግረዋል፡፡ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ከአሁን ቀደም በየወሩ ለብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት 58 ሚሊየን ብር ድጎማ በማድረግ ላይ ሲሆን አሁን ደግሞ ለአውቶቡሶች ኪራይ 63 ሚሊየን ብር በጠቅላላው 121 ሚሊዮን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ምክትል ከንቲባዋ አመልክተዋል፡፡

Published in አስተዳደር
Vrydag, 09 Oktober 2020 09:02

ኢትዮጵያውያን ነን!!

1.  ኢትዮጵያ መኩርያዬ ፤ህዝቦቿ መድመቂያዬና ሃብቴ

እርስ በእርስ የምንከባበር የአንዱ ህመም ለሌላው የሚሰማን፤ አንዱ የሌላውን ባህል የምንወድ፤ በማንነታችን የምንከባበር እንደውም  እንደ ቤተሰብ የምንተያይ፤  ብዙ ቋንቋ ኖሮን ሃሳባችን አንድ የሆነ ፤ብዙ መልክ ኖሮን ልዩነት ሳይሆን ህብረታችን የሚበረታ አንድ ታላቅ ህዝብ ነን!

2.  አብሮነታችንና ፍቅራችን አሸናፊ ነው!

#our love is victorious

የህዝቦች ፍቅር መተሳሰብና አንድነት ከፖለቲከኞች ሴራ እና ከፋፋይ አጀንዳ በርትቶ ትናትን ወደዛሬ አሻግሮናል፡፡ ነገም በድል የሚወጣ በመከባበር ላይ የተመሰረተ  እውነተኛ የህዝቦች መፈላለግ፡- ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡

Published in አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 4 መደበኛ ስብሰባው በህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል የሚታየውን የነዋሮዎች አቤቱታ እና እንግልት ለመፍታት በቀረበ አማራጭ ሃሳቦች ዙሪያ በመወያየት ውሣኔ አስተላልፏል፡፡ካቢኔው በሰጠው ውሳኔ መሰረትም በልዩ ሁኔታ 560 የከተማ አውቶቡሶች በኪራይ ቀርበው የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ወስኗል።

Published in አስተዳደር

የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል ከንጋቱ ጀምሮ በሆራ አርሰዴ በተከናወነ ስነስርዓት ተከበረ።የበዓሉ ስነ ስርዓት በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባገዳዎች ምርቃት ነው የተጀመረው፡፡በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሆራ አርሰዴ በማቅናት በባህሉ መሰረት ለፈጣሪያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የኢሬቻ በዓል የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።

Published in አስተዳደር

በፎረሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ህዝብ እሴት የሆኑ ባህሎችን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገር የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል ።በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችን መጎልበትና ደምቆ መታየት አለባቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የገዳ ስርአትን በትምህርት ስርአት ውስጥ ለማካተት በተግባር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓልን በቀጣይ አመት በተሻለ እና በአማረ መንገድ ይከበር ዘንድ የዘንድሮውን በጥንቃቄ ማሳለፍ ያስፈልጋል ብለዋል።የገዳ ስርአት 2009 . አዲስ አበባ በተካሄደው 11ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች ጉባኤ ላይ በቅርስነት መመዝገቡ የሚታወስ ሲሆን የኢሬቻን በዓል በተሻለ ለማስተዋወቅ እና በማይዳሰሱ ቅርስነት ለማስመዝገብ ሌሎች ዓለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ፎረሞች እንደሚካሄዱ በፎረሙ ላይ ተገልጿል

Published in አስተዳደር

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣የጽዳት ሰራተኞች እና ከፊንፊኔ ዙሪያ ካሉ የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተውጣጡ ወጣቶች በጽዳች ዘመቻው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክረታሪያት ኃላፊ አልፊያ ዮሱፍ የሆራ ፊንፊኔ ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት መርሃ ግብር ላይ ለተሳተፉ የከተማችን ወጣቶች የጽዳት ሰራተኞች እንዲሁም የአጎራባች ከተማ ወጣቶች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት ማሳያ እና ተምሳሌት መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ አልፊያ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በኮቪድ 19 ምክንያት የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት በወሰነው መሠረት በውስን ሰዎች እንደሚከበር ገልጸዋል።

Published in አስተዳደር

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ እንዲሁም ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ኢሬቻ የሚከበርበትን ስፍራ ጎብኝተዋል ።የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጥንቃቄ ጋር በተያያዘ በውስን ሰዎች እንደሚከበር የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ በጉብኝታቸው የበአሉ ማክበሪያ ስፍራ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።የኢሬቻ በዓል ሲከበር ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት እና ህዝቡም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ወይዘሮ አዳነች ጥሪ አቅርበዋል።

Published in አስተዳደር

"የኢሬቻ በዓል አከባበር እና የሴቶች ሚና" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ኦሮሚያ ሴቶች ማህበር ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከንቲባዋ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ማሾ ኦላና እና ከአስሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል።የኢሬቻ ክብረ በአል ከገዳ ስርዓቶች ውስጥ አንዱ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች ይህ የሰላም እና የምስጋና በዓል ባህላዊ እሴቱ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ሴቶች ትልቅ ሚና አላቸው ብለዋል።

Published in አስተዳደር

በየዓመቱ መስከረም 19 የሚከበረው የዓለም የልብ ቀንን ምክንያት በማድረግየተሰበሩ ልቦችን ከልብ እንጠግንበሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት የመጀመርያ ቀን ላይ በመገኘቴ ተደስቻለው / ሄለን እና የስራ ባልደረቦቻቸውን ጊዜያቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ሰዓታቸውን ከልብ ሰጥተዋልና ከልብ የሆነ ምስጋና እና አድናቆቴን ልሰጥ እወዳለሁ። የከተማችን አስተዳደርም ይህንን የህዝባችንን ህይውት የሚያድን ስራ የምንረዳ፣የምንደግፍ እና የምናበረታታ መሆናችንን አረጋግጣለው። በርቱ!

Published in አስተዳደር