open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ጠቅላይ ሚኒስትር / ዐቢይ አህመድ የጀግና አቀባበል ስነ ስርዓት ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡:የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው ዕለት በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ተገኝተው የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን መቀበላቸው ይታወሳል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፕሬስ ሴክሪታሪያት ሓላፊ ወይዘሪት ፌቨን ተሾመ በነገው ዕለት የሚደረገውን የአቀባባል ስነስርዓት አስመልከተው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከኖርዌይ ኦስሎ ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ስነ-ስርዓት ይደረግላቸዋል ብለዋል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የቀጥታ ድጋፍ ስራን በቅርቡ ለማስጀመር ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፍቃድ ማህበራት ውይይት አደረጉ፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በከተማዋ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዲሰራጩ በሚያስችልበት ሁኔታዎች ዙሪያ በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ የበጎ ፍቃድ ማህበራት ጋር ተነጋግረዋል፡፡