open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ መድኃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከአስሩ ክፍለ ከተሞች የተገኙ ባለድርሻ አካላት፣ የሐይማኖት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ ሚዲያዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች በተገኙበት፣  ትንባሆንና አደንዛዥ ዕፅን በተመለከተ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ቲአትርና ባህል አዳራሽ አካሂዷል፡፡

 በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር  ያደረጉት የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር  ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወረቲ፣ ሀገራችን በጤና ፖሊሲዋ ትምባሆና አደንዛዥ ዕፅን አስመልክቶ በአዋጅና በደንብ አካታ፤ ትልቅ ግምት እንዲሰጠው በመስራት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

 በቁጥጥር መመሪያውም በትምህርት ተቋማት፣ በጤና ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በባርና ሬስቶራንቶች፣ በመጓጓዣ አገልግሎቶች፣ በመዝናኛ ቦታዎችና ህዝብ በሚሰበሰብባቸው አካባቢዎች ሲጋራ ማጨስና ዕፅ መጠቀም በህግ እንደሚያስጠይቅም ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

 

(አዲስ አበባ፣ከንቲባ ጽ/ቤት)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት፤ «በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ንቅናቄ የሴቶችን ሁለንተናዊ  ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን!» በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ42ኛ ጊዜ በዓለም ለ1መቶ ሰባተኛ ጊዜ የተከበረዉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ፤  መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም  በከተማዋ ምክር ቤት አዳራሽ በመገኘት የግማሽ ቀን ዉይይት አድርገዋል፡፡

 

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት  የሀገር ውስጥ ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካሳ ወልደሰንበት፤ ሴቶች እናቶች፣እህቶች እና ሚስቶች እንደመሆናቸው  በማህበራዊ፣  በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ እንቅስቃሴው ያበረከቱትና የሚያበረክቱት ጉልህ ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ተሳትፎቸውን እና ተጠቃሚነታቸውን  ለማረጋገጥ ልናግዛቸው ይገባል በለዋል፡፡  ማርች 8ን ስናከብር ለሴቶችን መብት፣ ትግል፣ ተሳትፎና ተጠቃነታቸውን  ለማሳደግ ሁሉም የከንቲባ ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኛ የበኩሉን እንዲወጣ ሲሉም  መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡