open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራሽን ቢሮ በአዲስ መልክ ባዘጋጃቸው ልዩልዩ መመሪያዎችና የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከባለድርሻና የህዝብ ክንፍ አካላት ጋር መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም በግሎባል ሆቴል ምክክር አድርጓል፡፡

 

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው፣   የኮንስትራክሽን ዘርፉ በከተማዋም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የማይተካ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የመጣ ዘርፍ እንደሆነ በማስታወስ፤ ለሀገሪቱ እድገትና ብልፅግና ጉልህ ድርሻ መያዙን  ጠቁመዋል፡፡

 

ዘርፉ እያበረከተ ያለው አስተዋፆኦ እንደተጠበቀ ሆኖ መስተካከልና መሻሻል ያለባቸው ህጎችና መመሪያዎች እንዳሉም መገንዘብ ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባዉ፣ ዘርፉ ከተማዋ በኮንስትራክሽን ስራ ለምታደርገው ግስጋሴ ማፋጠን  በየደረጃው የሚታዩ ማነቆዎች፣ ችግሮችና የአሰራር መመሪያዎች መስተካከል እንደሚኖርባቸዉ አሳስበዋል፡፡

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፣ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ያዘጋጀው ስምንተኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት፣ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ከየካቲት 26-30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በኢግዚቪሽን ማዕከል ተከብሯል፡፡

 

የቢሮው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ በላይ ከፍያለው፣ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዋናነት ሁለት ዓላማ አንግበው መቋቋማቸውን አስታውሰው፤ የመጀመሪያው መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና መስጠት ሲሆን ሌላው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የመስሪያ ቦታዎችን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ድጋፍ ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን ድጋፍ ማድረግ ኢንተርፕራይዞች ምርታማና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻሉንና በአራቱ ፓኬጆች ማለትም የካይዘን ስራ ብክነትን በመቀነስ ምርታማነትን መጨመር፤ ክህሎትን መሙላት፣ የንግድ ስራ አያያዝ፣ የመዝገብ አያያዝ አዋጭ የሆነ ምርት አምርተው ገበያውን እንዲያዩ ማድረግና የቴክኖሎጂ ሽግግር በእስትራተጂው እንደተቀመጠው፤ እስከ 2017 ዓ.ም ቴክኖሎጂን የመቅዳት ስራን በማከናወን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡