open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

ሁለት መቶ የእሳት ማጥፊያ ውሃ መቅጃ መሣሪያዎች /fire hydrants /በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ሊተከሉ ነው ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከከተማ እና ከህንፃዎች ዕድገት ጋር ተያይዞ እየሰፋ ከመጣውን የእሳት እና ተያያዥ አደጋዎች ለመቀነስ የእሳት ማጥፊያ የሚያገለግሉ ሁለት መቶ የውሃ መቅጃ መሣሪያዎች በተለያዩ አካባቢዎች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ።

 

የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ እንደገለፁት የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎቹ(fire hydrants) 8 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ ሲሆን፣ ከከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንና መንገዶች ባለሥልጣን ጋር በመቀናጀት በተመረጡ ቦታዎች ይተከላሉ።

 

የእሳት አደጋ ቃጠሎ በተነሳ ጊዜ ውሃ የሚገኘበት ሁኔታ ብቁ ስላልሆነና የከተማው መስፋፋትም የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች ያልተተከለባቸው በርካታ አካባቢዎች ስላሉ ቦታዎች ተለይተው እንደሚተከሉ ገልጸዋል፡፡

 

በመንገድ ግንባታ ምክኒያት ሊፈርሱ የነበሩ የታላቁ አንዋር መስጅድ አካል የሆኑ ሱቆች አይፈርሱም ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ / ታከለ ኡማ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሱቆቹ ዙሪያ ከአዲስ አበባ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኡለማዎች እና የቦርድ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ከዚህ ቀደም በህዝበ ሙስሊሙ ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከእምነቱ ተከታዮች እና ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ በደረሰባቸው ጉዳዮችሱመረ ዙሪያም ተነጋግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት የይዞታ ጥያቄዎችን ጨምሮ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሌሎች የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች ዙሪያ ከኢ/ ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡