open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች 12ኛውን የህፃናት ቀን ህዳር 22 ቀን 2010ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ የምክር ቤት አባላት መሰብሰቢያ አዳራሽ በታላቅ ድምቀት አክብረዋል፡፡

 

በዓሉ በከንቲባ ጽ/ቤት የሥርዓተ-ፆታ፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ማካተት የስራ ክፍል አዘጋጅነት  ተከብሯል፡፡

 

<< በሴቶችና ህፃናት  ላይ  የሚፈፀመው  ጎጂ  ልማዳዊ  ድርጊቶች  ይቁም !!! በሚል መሪ ቃል  በዓለም  ለ 28ኛ ጊዜ  በሀገራችን  ለ 12ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕፃናት ቀን ሁሉም የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የህፃናትን መብት መጠበቅ እንዳለባቸው የጽ/ቤቱ ተወካይና የካቢኔ ጉዳዮች ልዩ ረዳት አቶ ዳዊት ምንዳዬ በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት ገልፀዋል፡፡

 

በዕለቱ የህፃናት መብትን አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የሴቶችና ህፃናት ቢሮ የህፃናት መብትና ደህንነት ማስከበር ባለሙያ አቶ ተሸመ ማሴቦ ሲሆኑ ከተማ አስተዳደሩ በዚህ በያዝነው 2010 በጀት ዓመት ለህፃናት መብት መከበርና በጎዳና የወደቁ ህፃናት ላይ በልዩ ትኩረት በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም ዜጋ የህፃናት መብትን የዘር፣ የሀይማኖት፣የቀለምና የዕድሜ ልዩነት ሳያደርግ በእኩል ፍቅር መጠበቅና መንከባከብ እንዳለበትም ገልፀዋል፡፡ የከንቲባ ጽ/ቤት ሰራተኞችም አስር ህፃናት ከደመወዛቸው በመቁረጥ እየረዱ መሆኑንም ለሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ብሎም ለሀገራችን ህዝብ ጭምር ትልቅ አርያነት ነው በማለት ጨምረው ገልፀዋል፡፡

 

አቶ ተሾመ ህፃናትን ለመርዳት አምስት ዓይነት የመርጃ መንገዶችን ማለትም ማህበረሰብ አቀፍ፣ ስፖንሰር ሺፕ፣ጉዲፈቻ፣ ዕርዳታ ማሰባሰብና ተቋም ማስገባት ናቸው ብለው በነዚህ መንገዶች መረዳዳት እንዳለብን  አሳስበዋል፡፡ ሰነዱም የተለያዩ ጥያቄዎችን፣ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን ያስተናገደ ሲሆን ለጥያቄዎችም የዕለቱ ክብር እንግዳ አቶ  ተሾመ ማሴቦ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል፡፡

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፈረንሳይዋ  ፅዳት ውበትና ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ከፈረንሳይዋ ሊዮንከመጡ  ልዑካንና  ከሚመለከታቸው የዩንቪርስቲ ምሁራን፣ የቢሮ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የሶስት ቀን ወርክ ሾፕ ከህዳር 19 – 21 ቀን 2010 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል አካሂዷል

 

 በወርክ ሾፑ ላይ ከአስር በላይ  ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን የአዲስ አበባን  ፓርኮች፣ ባዶ ቦታዎችና ጎዳናዎችን አረንጓዴ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ  የአዲስ አበባ ፅዳትና ውበት ዘላቂ ማረፊያ  ቢሮ ልዩ ትኩረት የሰጠበት ወርክሾፕ እንደነበረ ተመልክቷል፡፡

 

በቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፎችና ፕሮጀክቶች ላይ  በስድስት ቡድን ተመድበው በተጎበኙ ፓርኮችና አረንጓዴ ቦታዎች ጥልቅና መደረግ ያለባቸው ነገሮች ላይ ውይይት ተደርጓል፣ የሚታዩ ችግሮችንም ለማጥፋትና በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት የባለሙያዎች ሀሳብ ተንሸራሽሮበታል፡፡ በአዲስ አበባ በሚገኙ 16 ወንዞች ዙሪያም አሁን ካለበት መርዛማነትና ቆሻሻነት በማፅዳት ድሮ ለዋናና ለአልባሳት  እጥበት ይጠቅሙ  እንደነበር ለማድረግ አምስት ወንዞች ላይ የሚፅዳትና ተፈጥሮአዊ ቀለማቸውንና ውበታቸውን ይዘው ጥቅም እንዲሰጡ ወደ ወንዞች የሚለቀቁ የመፀዳጃ ቤት ቆሻሻና ፈሳሽ ቆሻሻዎች ነፃ የማድረግ ስራ እየተሰራ  እንደሆነ በቀጣይም 16 ቱንም የአዲስ አበባ  ወንዞች ፅዱ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን  የውበትና ፅዳት  ዘላቂ ማረፊያ ቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ተናግረዋል፡፡

 

አረንጓዴ ተክሎች የሰው ልጅ ትንፋሽ ናቸው እነሱ  ከሌሉ  መተንፈስ እናቆማለን ስለዚህ ለህብረተሰባችን የግንዛቤ ስራ መስራትና ጥበቃ እንዲያደርግ ለራሱ በህይወት  መኖር  እንዲሰራ መደረግ ይኖርበታል፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ከተባበርንና በጋራ ከሰራን የማይቻልና የማንሰራው ነገር የለም ተዓምር መፍጠር  የምንችል ህዝቦች ነን ያሉት ደ/ር ፋንታው ወሰን የወንዶች ገነት  የዩንቨርስቲ ተወካይ  ናቸው፡፡