open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ የፍራፍሬ ችግኝ ተከሉ፡፡የዓለም የምግብ ፕሮግራም 2050 እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 70በመቶ የምግብ አቅርቦት በከተማ ግብርና እንዲሸፈን ፕሮጀክት ቀርፆ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ ግብርና ማደግ የጤናም የኢኮኖሚም ፋይዳ ያለው መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠርም የከተማ ግብርናን ማሳደግ አንዱ መንገዳችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማም ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዛሬው ዕለት በመዘጋጃ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ የፖም /አፕል/ ፍራፍሬ ችግኝ ተክለዋል፡፡

 

 

 የከተማ አስተዳደሩ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ለነዋሪው ተጨማሪ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡በከተማዋ ውስጥ የከብት እርባታን ጨምሮ በፍራፍሬ ምርት ንብ ማነብ እንዲሁም አትክልትን በማምረት ስራ ላይ ከሁለት በላይ የሚሆኑ ወጣቶችን እና እናቶችን በማደራጀት ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ የከተማው የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው የከተማ ግብርና ነዋሪው የተጎዳ አከባቢን መልሶ እንዲያገግም ከማድረግ በተጨማሪ የራስ የምግብ ፍጆታን በመሸፈን ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡