open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

 

/ ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን የግንባታ መጓተትና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ዉይይት ከዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር አድርገዋል

በዉይይት መድረኩ ላይ በሶስት ክፍለከተሞች ማለትም በቦሌ አራዳ እና ቂሪቆስ ክፍለከተማ በሚገኙ 17 የሚሆኑ የተለያዩ ግንባታዎች ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡የዉይይቱ ተሳታፊዎች የባንክ ብድር አቅርቦትን ጨምሮ ከሊዝ አዋጅና መመሪያ እንዲሁም የመሰረተ ልማት ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር እንዲሁም ሌሎች ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን በዋናነት አንስተዋል።ግንባታዎቹ የከተማው አንጡራ ሀብት ናቸዉ ያሉት / ታከለ ኡማ በግንባታው ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 

/ ታከለ ኡማ የትራፊክ ክፍያን በዘመናዊ መንገድ ለመቀየር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዘርፉ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የትራፊክ ክፍያዎች "ለሁሉ" አገልግሎት ከተቋረጠ በኃላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ይህም አሽከርካርዎች እንዲጉላሉ እና ረዥም ወረፋ እንዲጠብቁ ምክንያት ሆኗል፡፡ይሄን አሰራር በዘመናዊ መንገድ ለመቀየርም የከተማ አስተዳደሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡