open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሐምሌ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤው፣ 31ኛውን የከተማዋን ከንቲባ ሹመት አጽድቋል፡፡ በከንቲባነት ሹመታቸው ያለፉትን አምስት አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ድሪባ ኩማ የሹመት ጊዜያቸው በማለቁ ኃላፊነታቸውን ለከንቲባ ታከለ ኡማ በንቲ (ኢንጂነር) አስረክበዋል፡፡

 አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ፤ የምክር ቤት አባል ባለመሆናቸዉ፣ ለጊዜዉ በምክትል ከንቲባነት ተሰይመዉ የዋና ከንቲባነቱን ሥራ  ያከናዉናሉ፡፡

 በተያያዘም ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በማድረግ ሁለት ሹመቶችንም ሰጥቷል። በዚህም መሰረት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና  ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) በምክትል ከንቲባ አድርጎሾመዋል።

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት) 77ኛው የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል በዓል የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት፤ በአራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም በድምቀት ተከብሯል፡፡

 

በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትና የአርበኞች የበላይ ጠባቂ  ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)  በንግግራቸው ወቅት፣ አያቶቻቻንና አባቶቻችን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የመጣውን የዘመኑን ኃይል ወራሪውን ፋሺስት የኢጣሊያ ሠራዊት በጦር፣  በጎራዴና በጋሻ በአድዋ አውደ-ውጊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን በማሸነፍ፤ ሀገራቸውን ከቅኝ ግዛት ለመታደግ ችለው፤ ለመላው የአለም ጥቁር ህዝብ ምሳሌ  አድርገውናል ሲሉ ዘክረዋቸዋል፡፡

 

ሚያዝያ 27 ቀን 2010 ዓ.ም  የምናከብረው  የድል ቀን ጣልያን በድጋሚ በአድዋ የደረሰበትን አሳፋሪ ሽንፈት ለመበቀል፣ ከ45 ዓመታት በኋላ  ሀገራችንን ለመውረር  በመጣበት ወቅት፣ የወቅቱ ኢትዮጵያዉያን  አርበኞች አያቶቻችን፣ አባቶቻቸው እና እናቶቻቸው በአድዋ የፈጸሙትን ገድል በማስታወስ እና ኢትዮጵያውያን በጀግንነት በሀገር ጉዳይ የማንደራደር  በመሆናችን ምንም እንኳን በዘመናዊ መሳሪያ እራሱን  አስታጥቆና ከአድዋው  ጦርነት ተምሮ ወታደሩን የበለጠ  አሰልጥኖ  ቢመጣም፤ በየዱር ገደሉና በየጫካው ፋታ በማሳጣት፣ ለአምስት  አመታት በአርበኝነት የአድዋውን ድል የደገሙበት በመሆኑ ታላቅ ክብር ለአርበኞቻችን ይገባቸዋል ብለዋል፡፡