open

ዜና

  Tuiste/ሚዲያ/ዜና

 

(አዲስ አበባ፣ ከንቲባ ጽ/ቤት)፣ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ያዘጋጀው ስምንተኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት፣ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች ከየካቲት 26-30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ በኢግዚቪሽን ማዕከል ተከብሯል፡፡

 

የቢሮው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ በላይ ከፍያለው፣ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በዋናነት ሁለት ዓላማ አንግበው መቋቋማቸውን አስታውሰው፤ የመጀመሪያው መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና መስጠት ሲሆን ሌላው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማትን ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የመስሪያ ቦታዎችን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት ድጋፍ ማድረግ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን ድጋፍ ማድረግ ኢንተርፕራይዞች ምርታማና በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻሉንና በአራቱ ፓኬጆች ማለትም የካይዘን ስራ ብክነትን በመቀነስ ምርታማነትን መጨመር፤ ክህሎትን መሙላት፣ የንግድ ስራ አያያዝ፣ የመዝገብ አያያዝ አዋጭ የሆነ ምርት አምርተው ገበያውን እንዲያዩ ማድረግና የቴክኖሎጂ ሽግግር በእስትራተጂው እንደተቀመጠው፤ እስከ 2017 ዓ.ም ቴክኖሎጂን የመቅዳት ስራን በማከናወን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በከተማዋ 247 ሺህ  ወላጅ ያጡ ህፃናትና ወጣቶች አሉ

 

 (አዲስ አበባ፣ ከንቲባ /ቤት) 70 በላይ ለሚሆኑ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  /ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በኤች አይ ኤድስ ላይ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስልጠና  የካቲት 30 ቀን 2010 . በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡

 

ስልጠናውን ያዘጋጀው የጽ/ቤቱ ስትራቴጅክ ዕቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማና ሪፖርት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ከስርዓተ ፆታ፣ ወጣቶች ህፃናትና ጉዳይ ማካተት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ሲሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ኤች አይ መከላከያና መቆጣጠሪያ /ቤት  በተገኙ ባለሙያ ገለፃ ቀርቧል፡፡

 

ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው ተቋማት በጀት ይዘው ሰራተኛውንና ቤተሰቡን ከኤች ኤይ ኤድስ ለመከላከል የሚያስችለውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን ባለሙያው አቶ ወንድሙ ደንቡ አመላክተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን 700 መቶ ሺህ በላይ ህዝብ  ኤች አይ ቫይረስ  በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህም ከአንድ በመቶ በላይ የኤች አይ ስርጭት መጠን ስላለው በጥናቱ መሰረት ሀገሪቱ በወረርሽኝ ደረጃ እንደምትገኝ ያመለክታል ብለዋል፡፡

 

ለአብነት ያህል በአዲስ አበባ  1መቶ ሰዎች አምስቱ  የኤች አይ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይም በደቡብ ክልል 1 መቶ ሰዎች ውሰጥ አንዱ ቫይረሱ  በደሙ  ውስጥ እንደሚገኝና ይህም ስርጭቱ ከክልል ክልል መለያየቱን እንደሚሳይ የባለሙያው ገለፃ ጠቁሟል፡፡ የኤች አይ   ስርጭትን  አስመልክቶ ሴቶች 20 በመቶ  በላይ ከወንዶች ብልጫ ለኤች አይ የመጋለጥ እድል እንዳላቸውና ይህም ተጋላጭነት በደረጃ ሲቀመጥ ሴተኛ አዳሪዎች ከመቶ 25 ቫይረሱ በደማቸው ሲኖር፤ ተንቀሳቃሽ  ሰራተኞች 5.7 ከመቶ፣ ረዥም ርቀት  አሽከርካሪዎች 4.9 ከመቶ፣ ህግ ታራሚዎች 4.2 ከመ፣ በግንባታ ዘርፍ  የተሰማሩ 2.9 ከመቶ እንደሆነ ለስልጠናው የተሰናዳው ሰነድ አመላክቷል፡፡