በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገለፁት።
በተለይ በምርጫ ወቅት ዜጎች በልዩ ልዩ መንገዶች ተሳትፎአቸውን ሊያረጋግጡ ይችላሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካርድ ወስደው በሰላማዊ መንገድ ለመምረጥ ራስን ከማዘጋጀት በዘለለ፣ በሲቪክ ማኅበራት አማካኝነት የምርጫው ሂደት ግልጽና ተአማኒ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል ነው ያሉት።…