በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ውስጥ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማስጨረስ በሚል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማያውቃቸው ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም አገልግሎቱን ለማግኘት በቀረቡበት ወቅት የያዙት ሰነድ ሀሰተኛ ወይም ትክክለኛ የተቋሙ ሰነድ አለመሆኑን በማረጋገጥ ወዲያውኑ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ እንዲያዙ ተደርገዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአሁኑ ሰዓት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ በርካታ የሪፎርም ፣ የአደረጃጀትና አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በዚህም መሠረት ዋናዋናዎቹን አሰራሮች በኦንላይን ከሰው ንክኪ ነፃ እንዲሁም ቀሪዎቹን ደግሞ የዜጎችን ምልልስና እንግልት በእጅጉ ቀለል በሚያደርግ መልኩ ተግባራዊ አድርጓቸዋል።
ለተለያዩ የማጭበርበር ስራዎች የማይመች ሲሆን ከተገኘም በቀላሉ መለየትና መያዝ የሚያስችልም መሆኑ ተጠቅሷል።
የከተማው ነዋሪ ከእንዲህ አይነት ተግባር ውስጥ ካሉ አጭበርባሪዎች ርቆ እና ተቆጥቦ በህጉ መሠረት ብቻ መብቱን በቀላሉ እና በፈለገ ሰዓት ያለምንም ምልልስና እንግልት አገልግሎት እንዲያገኝ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ ከተማችንን ከህገወጦች እንዲጠብቅ የከተማ አስተዳደሩ ያሳስባል።
*ዘገባውን ያደረሰን የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።