17ኛውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በሀዋሳ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ከማለዳው ጀምሮ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ታድመዋል።
ህጻናትና ወጣቶች የተለያዩ ትርኢቶችን እያቀረቡ ሲሆን የሀገር መከላከያ ማርሽ ባንድም የተለያዩ ጣእመ ዜማዎችን በማቅረብ ለበአሉ ድምቀት እየሰጠ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከንቲባዎች ተገኝተዋል።