ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ከአምስት ሳምንታት በፊት ዓመታዊውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማስመለከት የቤት እድሳት መርኃ ግብር በአዋሬ አካባቢ አስጀምረን ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት እድሳታቸው የተጠናቀቀ ቤቶችን አረጋውያን አስረክበዋል።
ሁሉም ዜጎች ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች እፎይታ ለመስጠት በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።