በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ሲካሄድ የዋለው ህዝብን የማዳመጥ መድረክ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሰብሳቢው የተነሱ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ አጭር አስተያየታቸውን የሰጡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቤቱ የተሰጡትን አስተያቶች በሙሉ እደ ግብዓት እንደሚወሰዱ አረጋግጠው ‹‹ በ121 ወረዳና በ11 ክ/ከተማ እየተካሄዱ ባለው መድረክ ከሁሉም ሥፍራ የሚነሱ ጥያቄዎች በቂ ግብአት ይሰበሰባል ብለን እናምናለን ሁላችንም የየድርሻችንን ወስደን ጥያቄዎችን በሚገባቸው ቅደም ተከተል እየፈታን የምንዘልቅ ይሆናል ብለዋል፡፡
ትርከቶችንና ሰንደቅ-ዓለማና መሠል አጀንዳዎች በአገር አቀፍ ምክክሩ ላይ አጀንዳ ተደርገው ተይዘዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች በዚያም መፍትሔ ያገኛሉ ብለን እናምናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራሕ በበኩላቸው ለጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት አመራሮችን ማጥራት፣የተቋማትን አሰራር መፈተሽ፣ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፣ሌብነትን መታገል ፣ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የተመለከቱ ጥያቄዎችና ሌሎችንም ክሕዝቡ ጋር ተቀራርበን እየመከርን በጋራ እያረምን የምንሄደው የቤት ስራችን ይሆናል ብለዋል፡፡
አግላይነትን በማስወገድ፣ልዩነትን ማጥበብ እና ሕዝባዊ አንድነታችንን በማጠናከር በግዜ ሂደት ሕዝባችንን በማሣተፍ ፈተናዎቻችንን በመሻገር ለጋጠሙን ችግሮችም መፍትሄ እየሰጠን የምንሄድ ይሆናል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ
እንደሀገር አቀፍ ከሕዝቦች የሚሰበሰቡ ጥያቄዎችን ወደ ዕቅድ በመለወጥ በሂደት ለተነሱ ጉዳዮች ተመጣጣኝ ምላሽ እየሰጠን እንሄዳለን ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ለስኬታማነቱም ሕዝባችን በሁሉም ረገድ ልያግዘን ይገባል ብለዋል።