የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ ፎርጅድ/ሃሰተኛ መታወቂያ / የሚያባዙና መታወቂያውን የሚያሰሩ 7 ተጠርጣሪ ግልሰቦች ናቸው እጅ ከፍንጅ በፖሊስ የተያዙት፡፡
የሃሰተኛ መታወቂያ አታሚዎቹ ፒያሳ ሮቤል የጽህፈት መሳሪያ መሸጫ ተብሎ በሚጠራው ድርጅት ውስጥ ነው ሲያትሙ የተያዙት፡፡
ሃሰተኛ መታወቂያዎቹ የሚያባዙ ግለሰቦች በአንድ መታወቂያ 10 ሺህ ብር እየተቀበሉ እንደሚሰሩም ታውቋል፡፡
የግለሰቦች ስም እና የክፍለከተማ ስም ብቻ እየቀያየሩ ሃሰተኛ መታወቂያ እያዘጋጁ ብር እንደሚቀበሉ ነው መገንዘብ የተቻለው፡፡
የሀሰተኛ መታወቂያዎቹ የተለያዩ ወንጀሉችን ሊፈጸምባቸው የሚችሉ እንደሆነም ፖሊሲ ገልጿል፡፡
ከተጠርጣሪዎች ጋር በኤግዚቢትነት የፍትህ ሚኒስቴትር፤የኢትየጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ፤ የደቡብ ክልል ሀድያዞን ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ፤የፌደራለ ሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ፤ ወዘተ የሚሉ ማህተሞች ተይዘዋል፡፡
በከተማችን የሚፈጸሙ የስርቆትና ሌሎች ወንጀሎች ለመቆጣጠር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን አየሰራ ነው፡፡
ዛሬም የሃሰተኛ መታወቂያ ሲያባዙ የተያዙት ግለሰቦች በከተማችን ነዋሪዎች ጥቆማ ተደርጐ በከተማ አስተዳደሩ በፀጥታ ዘርፍና በፖሊስ ክትትል ተደርጐ ወንጀል ፈጻሚዎቹ በቁጥጥር እንዲውሉ ሆኗል፡፡
በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች ሃሰተኛ ሰነድ የሚሰሩ ግለሰቦች መረጃ ለፖሊስ በመስጠት ወንጀለኞችን በማጋለጥ የከተማችን ሰላም ማረጋገጥ ይገባል ተብሏል፡፡